Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 14:42 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

42 ሳኦ​ልም፥ “በእ​ኔና በዮ​ና​ታን መካ​ከል ዕጣ አጣ​ጥ​ሉን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዕጣ ያወ​ጣ​በ​ትም ይሞ​ታል” አላ​ቸው። ሕዝ​ቡም ሳኦ​ልን፥ “እን​ዲህ ያለ ነገር አይ​ሆ​ንም” አሉት፤ ሳኦ​ልም ሕዝ​ቡን እንቢ አላ​ቸው። በእ​ር​ሱና በልጁ በዮ​ና​ታን መካ​ከ​ልም ዕጣ አጣ​ጣሉ። ዕጣ​ውም በልጁ በዮ​ና​ታን ላይ ወጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

42 ሳኦልም፣ “በእኔና በልጄ በዮናታን መካከልም ዕጣ ጣሉ” አላቸው። ዕጣውም በዮናታን ላይ ወደቀ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

42 ሳኦልም፥ “በእኔና በልጄ በዮናታን መካከልም ዕጣ ጣሉ” አላቸው። ዕጣውም በዮናታን ላይ ወደቀ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

42 ከዚህም በኋላ ሳኦል “በእኔና በልጄ በዮናታን መካከል ዕጣ ጣሉ” አለ፤ ዕጣውም በዮናታን ላይ መጣ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

42 ሳኦልም፦ በእኔና በልጄ በዮናታን መካከል ዕጣ ጣሉ አለ። ዮናታንም ተያዘ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 14:42
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሳኦ​ልም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ ለእኔ ለባ​ሪ​ያህ ዛሬ ያል​መ​ለ​ስ​ህ​ልኝ ስለ ምን​ድን ነው? ይህች በደል በእኔ፥ በልጄ በዮ​ና​ታ​ንም እንደ ሆነች አቤቱ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ ተና​ገር። ዕጣው ይህን የሚ​ገ​ልጥ ከሆነ ለሕ​ዝ​ብህ ለእ​ስ​ራ​ኤል እው​ነ​ትን ግለጥ፥” አለ። ዕጣም በዮ​ና​ታ​ንና በሳ​ኦል ላይ ወጣ፤ ሕዝ​ቡም ነፃ ወጣ።


ሳኦ​ልም ዮና​ታ​ንን፥ “ያደ​ረ​ግ​ኸ​ውን ንገ​ረኝ” አለው፤ ዮና​ታ​ንም፥ “በእጄ ባለው በበ​ትሬ ጫፍ ጥቂት ማር በር​ግጥ ቀም​ሻ​ለሁ፤ እነ​ሆኝ፥ እሞ​ታ​ለሁ” ብሎ ነገ​ረው።


እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “ይህ ክፉ ነገር በማን ምክ​ን​ያት እንደ አገ​ኘን እና​ውቅ ዘንድ ኑ፤ ዕጣ እን​ጣ​ጣል” ተባ​ባሉ። ዕጣም ተጣ​ጣሉ፤ ዕጣ​ውም በዮ​ናስ ላይ ወደቀ።


በዘ​ን​በ​ሪም ወገን ምል​ክት ታየ፤ የዘ​ን​በ​ሪም ቤተ ሰብ እያ​ን​ዳ​ንዱ ተለየ፤ ከይ​ሁ​ዳም ወገን በሆነ በከ​ርሚ ልጅ በዘ​ን​በሪ ልጅ በዛራ ልጅ በአ​ካን ላይ ምል​ክት ታየ።


የበደለኛ ሰው በደሉ ሁሉ ወደ ጕያው ይመለሳል። ጽድቅ ሁሉ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።


ዕጣ ክርክርን ያስተዋል፥ በኀያላንም መካከል ይለያል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች