Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 14:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ነገር ግን ወደ እኛ ውጡ ቢሉን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ጃ​ችን አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና እን​ወ​ጣ​ለን፤ ምል​ክ​ታ​ች​ንም ይህ ይሆ​ናል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ነገር ግን፣ ‘ወደ እኛ ውጡ’ ካሉን፣ እግዚአብሔር እነርሱን በእጃችን አሳልፎ የሰጠን ለመሆኑ ምልክቱ ይህ ስለ ሆነ፣ ወደ እነርሱ እንወጣለን።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ነገር ግን፥ ‘ወደ እኛ ኑ’ ካሉን፥ ጌታ እነርሱን በእጃችን አሳልፎ የሰጠን ለመሆኑ ምልክቱ ይህ ስለሆነ፥ ወደ እነርሱ እንወጣለን።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ነገር ግን ‘ወደ እኛ ኑ’ ቢሉን፥ ወደ እነርሱ እንሄዳለን፤ ይህም እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን ላይ ድልን የሚያቀዳጀን ለመሆኑ ምልክት ይሆንልናል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ነገር ግን፦ ወደ እኛ ውጡ ቢሉን እግዚአብሔር በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶአቸዋልና እንወጣለን፥ ምልክታችንም ይህ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 14:10
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እን​ስ​ራ​ሽን አዘ​ን​ብ​ለሽ ውኃ አጠ​ጭኝ የም​ላት እር​ስ​ዋም፦ ‘አንተ ጠጣ፥ ግመ​ሎ​ች​ህን ደግሞ እስ​ኪ​ረኩ አጠ​ጣ​ለሁ’ የም​ት​ለኝ ድን​ግል፥ እር​ስዋ ለባ​ሪ​ያህ ለይ​ስ​ሐቅ ያዘ​ጋ​ጀ​ሃት ትሁን፤ በዚ​ህም ለጌ​ታዬ ለአ​ብ​ር​ሃም ምሕ​ረ​ትን እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ አው​ቃ​ለሁ።”


ኢሳ​ይ​ያ​ስም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረ​ውን ነገር እን​ዲ​ፈ​ጽ​መው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ምል​ክቱ ይህ ይሆ​ን​ል​ሃል፤ ጥላው ዐሥር ደረጃ ወደ ፊት ይሂ​ድን? ወይስ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላው ይመ​ለስ?” አለ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን ተና​ገ​ረው፤ እን​ዲህ ሲል፥ “በእ​ው​ነት እኔ ከአ​ንተ ጋር እሆ​ና​ለሁ፤ እኔም እንደ ላክ​ሁህ ይህ ለአ​ንተ ምል​ክት ይሆ​ን​ሃል፤ ሕዝ​ቡን ከግ​ብፅ በአ​ወ​ጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ል​ካ​ላ​ችሁ” አለው።


ጌዴ​ዎ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “እንደ ተና​ገ​ርህ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በእኔ እጅ ታድን እንደ ሆነ፥


የሚ​ና​ገ​ሩ​ት​ንም አድ​ም​ጣ​ቸው፤ ከዚ​ያም በኋላ እጆ​ችህ ይበ​ረ​ታሉ፤ ወደ ሰፈ​ርም ትወ​ር​ዳ​ለህ” አለው። እር​ሱም ከሎ​ሌው ፋራን ጋር ከሰ​ፈሩ በአ​ንድ ወገን የአ​ምሳ አለቃ ጦር ወደ ሰፈ​ረ​በት ወረደ።


እነ​ዚ​ህም ምል​ክ​ቶች በደ​ረ​ሱህ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነውና እጅህ የም​ት​ች​ለ​ውን ሁሉ አድ​ርግ።


እነ​ር​ሱም፦ እስ​ክ​ን​ነ​ግ​ራ​ችሁ ድረስ ርቃ​ችሁ ቈዩ ቢሉን ርቀን እን​ቆ​ማ​ለን፤ ወደ እነ​ር​ሱም አን​ወ​ጣም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች