Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 14:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በነ​ጋም ጊዜ፥ የሳ​ኦል ልጅ ዮና​ታን ጋሻ ጃግ​ሬ​ውን፥ “ና፤ በዚያ በኩል ወዳ​ለው ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሰፈር እን​ለፍ” አለው፤ ለአ​ባ​ቱም አል​ነ​ገ​ረ​ውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 አንድ ቀን የሳኦል ልጅ ዮናታን ወጣት ጋሻ ጃግሬውን፣ “ና በሌላ በኩል ወዳለው የፍልስጥኤማውያን ጦር ሰፈር እንሻገር” አለው። ይህን ግን ለአባቱ አልነገረውም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 አንድ ቀን የሳኦል ልጅ ዮናታን ወጣት ጋሻ ጃግሬውን፥ “ና በሌላ በኩል ወዳለው የፍልስጥኤማውያን ጦር ሰፈር እንሻገር” አለው። ይህን ግን ለአባቱ አልነገረውም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 አንድ ቀን የሳኦል ልጅ ዮናታን የጦር መሣሪያ የሚሸከምለትን ወጣት ጋሻ ጃግሬውን “ወደ ፍልስጥኤማውያን የጦር ሰፈር እንሻገር” አለው። ነገር ግን ዮናታን ይህን ጉዳይ ለአባቱ እንኳ አልነገረውም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 አንድ ቀንም እንዲህ ሆነ፥ የሳኦል ልጅ ዮናታን ጋሻ ጃግሬውን፦ ና፥ በዚያ በኩል ወዳለው ወደ ፍልስጥኤማውያን ጭፍራ እንለፍ አለው፥ ለአባቱም አልነገረውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 14:1
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ባልንጀራን አትመኑ፥ በወዳጅም አትታመኑ፥ የአፍህን ደጅ በብብትህ ከምትተኛው ጠብቅ።


ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ዋም፥ “አስ​ቀ​ድ​ማ​ችሁ በፊቴ ሂዱ፤ እነ​ሆም እከ​ተ​ላ​ች​ኋ​ለሁ” አለች። ይህ​ንም ለባ​ልዋ ለና​ባል አል​ነ​ገ​ረ​ች​ውም።


ስለ​ዚ​ህም በማ​ኪ​ማስ ጦር​ነት ጊዜ ሰይ​ፍና ጦር ከሳ​ኦ​ልና ከዮ​ና​ታን ጋር በነ​በሩ ሕዝብ ሁሉ እጅ አል​ተ​ገ​ኘም፤ ብቻ በሳ​ኦ​ልና በልጁ በዮ​ና​ታን ዘንድ ተገኘ።


ያን​ጊ​ዜም ሳኦል ሦስት ሺህ ሰዎ​ችን ከእ​ስ​ራ​ኤል መረጠ፤ ሁለ​ቱም ሺህ በማ​ኪ​ማ​ስና በቤ​ቴል ተራራ ከሳ​ኦል ጋር ነበሩ፤ አን​ዱም ሺህ በብ​ን​ያም ገባ​ዖን ከልጁ ከዮ​ና​ታን ጋር ነበሩ፤ የቀ​ረ​ው​ንም ሕዝብ እያ​ን​ዳ​ን​ዱን ወደ ድን​ኳኑ አሰ​ና​በተ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በእ​ርሱ ላይ አደረ፤ የፍ​የል ጠቦ​ትን እን​ደ​ሚ​ጥ​ልም ጣለው፤ በእ​ጁም እንደ ኢም​ንት ሆነ፤ ያደ​ረ​ገ​ው​ንም ለአ​ባ​ቱና ለእ​ናቱ አል​ተ​ና​ገ​ረም።


ጌዴ​ዎ​ንም ከባ​ሪ​ያ​ዎቹ ዐሥራ ሦስት ሰዎ​ችን ወስዶ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ለው አደ​ረገ፤ የአ​ባ​ቱ​ንም ቤተ ሰቦች፥ የከ​ተ​ማ​ዉ​ንም ሰዎች ስለ​ፈራ ይህን በቀን ለማ​ድ​ረግ አል​ቻ​ለም፤ ነገር ግን በሌ​ሊት አደ​ረ​ገው።


ከዚ​ያም ጥቂ​ቶች ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሰፈር ወደ ማኪ​ማስ መተ​ላ​ለ​ፊያ ወጡ።


ሳኦ​ልም በመ​ጌ​ዶን ባለው በሮ​ማኑ ዛፍ በታች በኮ​ረ​ብ​ታው ላይ ተቀ​ምጦ ነበር፤ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ረው ሕዝብ ስድ​ስት መቶ የሚ​ያ​ህል ሰው ነበረ።


ወስ​ዶም በላ፤ እየ​በ​ላም ሄደ፤ ወደ አባ​ቱና ወደ እና​ቱም ደረሰ፤ ሰጣ​ቸ​ውም፤ እነ​ር​ሱም በሉ፤ ማሩ​ንም ከአ​ን​በ​ሳው አፍ ውስጥ እን​ዳ​ወ​ጣው አል​ነ​ገ​ራ​ቸ​ውም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች