Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 13:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ተሻ​ግ​ረው ወደ ጋድና ወደ ገለ​ዓድ ምድር የሄዱ አሉ፤ ሳኦል ግን ገና በጌ​ል​ጌላ ነበረ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ፈር​ተው እር​ሱን መከ​ተ​ልን ትተው ተበ​ተኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ከዕብራውያንም አንዳንዶቹ ዮርዳኖስን ተሻግረው ወደ ጋድና ወደ ገለዓድ ምድር ሄዱ። ሳኦል ግን በጌልገላ ቈየ፣ ዐብሮት የነበረውም ሰራዊት ሁሉ በፍርሀት ይንቀጠቀጥ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ከዕብራውያንም አንዳንዶቹ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግረው ወደ ጋድና ወደ ገለዓድ ምድር ሄዱ። ሳኦል ግን ገና በጌልገላ ነበር፤ አብሮት የተሰለፈው ሠራዊት ሁሉ በፍርሃት ይንቀጠቀጥ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ከዕብራውያን መካከል አንዳንዶቹ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግረው ወደ ጋድና ወደ ገለዓድ ግዛቶች ሄዱ። ሳኦል ግን እስከዚህ ጊዜ ድረስ በጌልገላ ነበር፤ ከእርሱም ጋር የነበረው ሠራዊት ከፍርሃት የተነሣ ይንቀጠቀጥ ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ከዕብራውያንም ዮርዳኖስን ተሻግረው ወደ ጋድና ወደ ገለዓድ ምድር ሄዱ፥ ሳኦል ግን ገና በጌልገላ ነበረ፥ ሕዝቡም ሁሉ ተንቀጥቅጠው ተከተሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 13:7
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሁን እን​ግ​ዲህ፥ “የፈራ፥ የደ​ነ​ገ​ጠም ከገ​ለ​ዓድ ተራራ ተነ​ሥቶ ይመ​ለስ ብለህ በሕ​ዝቡ ጆሮ አውጅ” አለው። ከሕ​ዝ​ቡም ሃያ ሁለት ሺህ ተመ​ለሱ፤ ዐሥ​ርም ሺህ ቀሩ።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጠ​ላ​ቶ​ችህ ፊት የተ​መ​ታህ ያደ​ር​ግ​ሃል፤ በአ​ንድ መን​ገድ ትወ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ በሰ​ባት መን​ገ​ድም ከእ​ነ​ርሱ ትሸ​ሻ​ለህ፤ በም​ድ​ርም መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ የተ​በ​ተ​ንህ ትሆ​ና​ለህ።


ጸሐ​ፍ​ቱም ደግሞ ጨም​ረው፦ ማንም ፈሪና ልበ ድን​ጉጥ ሰው ቢሆን የወ​ን​ድ​ሞ​ቹን ልብ እንደ እርሱ እን​ዳ​ያ​ስ​ፈራ ወደ ቤቱ ተመ​ልሶ ይሂድ ብለው ለሕ​ዝቡ ይና​ገሩ።


“ይህ​ች​ንም ምድር በዚ​ያን ዘመን ወረ​ስን፤ በአ​ር​ኖ​ንም ሸለቆ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔር ጀምሮ የገ​ለ​ዓ​ድን ተራ​ራማ ሀገር እኩ​ሌታ፥ ከተ​ሞ​ቹ​ንም ለሮ​ቤ​ልና ለጋድ ነገድ ሰጠ​ኋ​ቸው።


ፊቴ​ንም አከ​ብ​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ፊት ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ፤ የሚ​ጠ​ሏ​ች​ሁም ያሸ​ን​ፉ​አ​ች​ኋል። ማንም ሳያ​ሳ​ድ​ዳ​ችሁ ትሸ​ሻ​ላ​ችሁ።


ሳኦ​ልም ሳሙ​ኤል እንደ ቀጠ​ረው ጊዜ ሰባት ቀን ቈየ፤ ሳሙ​ኤል ግን ወደ ጌል​ጌላ አል​መ​ጣም፤ ሕዝ​ቡም ከእ​ርሱ ተለ​ይ​ተው ተበ​ታ​ተኑ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴም እንደ ሰጣ​ቸው ከእ​ርሱ ከም​ናሴ ጋር የሮ​ቤ​ልና የጋድ ልጆች፥ በም​ሥ​ራቅ በኩል በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ሙሴ የሰ​ጣ​ቸ​ውን ርስ​ታ​ቸ​ውን ተቀ​በሉ።


ገለ​ዓ​ድ​ንም፥ የጌ​ሴ​ሪ​ያ​ው​ያ​ን​ንና የመ​ከ​ጢ​ያ​ው​ያ​ንን ዳርቻ ሁሉ፥ የአ​ር​ሞ​ን​ዔ​ም​ንም ተራራ ሁሉ፥ ባሳ​ን​ንም ሁሉ፥ እስከ ሰልካ ድረስ፥


ሳኦ​ልና እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ይህን የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውን ቃል በሰሙ ጊዜ እጅግ ፈሩ፤ ደነ​ገ​ጡም።


በሸ​ለ​ቆ​ውም ማዶና በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ የነ​በሩ እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች እንደ ሸሹ፥ ሳኦ​ልና ልጆ​ቹም እንደ ሞቱ ባዩ ጊዜ ከተ​ሞ​ቹን ለቅ​ቀው ሸሹ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም መጥ​ተው ተቀ​መ​ጡ​ባ​ቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች