Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 11:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ሳሙ​ኤ​ልም ሕዝ​ቡን፥ “ኑ፤ ወደ ጌል​ገላ እን​ሂድ፤ በዚ​ያም መን​ግ​ሥ​ቱን እና​ጽና” አላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ከዚያም ሳሙኤል ሕዝቡን፣ “ኑና ወደ ጌልገላ እንሂድ፤ ንግሥናውን እናጽና” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ከዚያም ሳሙኤል ሕዝቡን፥ “ኑና ወደ ጌልገላ እንሂድ፤ ንግሥናውንም እናጽና” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ሳሙኤልም “ሁላችንም ወደ ጌልጌላ እንሂድና ሳኦል ንጉሣችን መሆኑን እንደገና በይፋ እናረጋግጥ” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ሳሙኤልም ሕዝቡን፦ ኑ፥ ወደ ጌልገላ እንሂድ፥ በዚያም መንግሥቱን እናድስ አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 11:14
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በፊ​ቴም ወደ ጌል​ገላ ትወ​ር​ዳ​ለህ፤ እኔም እነሆ፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ርብ ዘንድ፥ የደ​ኅ​ን​ነ​ት​ንም መሥ​ዋ​ዕት እሠዋ ዘንድ ወደ አንተ እወ​ር​ዳ​ለሁ፤ እኔ ወደ አንተ እስ​ክ​መ​ጣና የም​ታ​ደ​ር​ገ​ውን እስ​ከ​ም​ነ​ግ​ርህ ድረስ ሰባት ቀን ትቈ​ያ​ለህ።”


በየ​ዓ​መ​ቱም ወደ ቤቴል፥ ወደ ጌል​ጌ​ላና ወደ መሴፋ ይዞር ነበር፤ በእ​ነ​ዚ​ያም በተ​ቀ​ደሱ ስፍ​ራ​ዎች ሁሉ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ይፈ​ርድ ነበር።


በነ​ጋ​ውም የአ​ዛ​ጦን ሰዎች ማለዱ፤ ወደ ዳጎ​ንም ቤት ገቡ፤ እነ​ሆም፥ ዳጎን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት በም​ድር ላይ በግ​ን​ባሩ ወድቆ አገ​ኙት፤ ዳጎ​ን​ንም አን​ሥ​ተው በስ​ፍ​ራው አቆ​ሙት።


ሳሙ​ኤ​ልም ለእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ሁሉ አለ፥ “የነ​ገ​ራ​ች​ሁ​ኝን ሁሉ ሰምቼ ንጉሥ አን​ግ​ሼ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


ንጉ​ሡም ተመ​ልሶ እስከ ዮር​ዳ​ኖስ ድረስ መጣ። የይ​ሁዳ ሰዎ​ችም ንጉ​ሡን ሊቀ​በሉ፥ ንጉ​ሡ​ንም ዮር​ዳ​ኖ​ስን ሊያ​ሻ​ግሩ ወደ ጌል​ገላ መጡ።


ነገር ግን ጌል​ገላ ፈጽሞ ትማ​ረ​ካ​ለ​ችና፥ ቤቴ​ልም እን​ዳ​ል​ነ​በ​ረች ትሆ​ና​ለ​ችና ቤቴ​ልን አት​ፈ​ልጉ፤ ወደ ጌል​ገ​ላም አት​ሂዱ፤ ወደ ቤር​ሳ​ቤ​ህም አት​ለፉ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች