Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 11:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ሳኦ​ልም፦“በዚ​ያች ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ስ​ራ​ኤል ድኅ​ነ​ትን አድ​ር​ጎ​አ​ልና ዛሬ አንድ ሰው አይ​ሞ​ትም” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ሳኦል ግን፣ “ይህ ዕለት እግዚአብሔር እስራኤልን የታደገበት ቀን ስለ ሆነ፣ በዛሬው ዕለት ማንም ሰው አይገደልም” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ሳኦል ግን፥ “ይህ ዕለት ጌታ እስራኤልን የታደገበት ቀን ሰለሆነ፥ በዛሬው ዕለት ማንም ሰው አይገደልም” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ሳኦል ግን “በዛሬው ቀን እግዚአብሔር እስራኤልን ስላዳነ ማንም ሰው መገደል የለበትም” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ሳኦልም፦ ዛሬ እግዚአብሔር ለእስራኤል ማዳን አድርጎአልና ዛሬ አንድ ሰው አይሞትም አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 11:13
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊ​ትም፥ “እና​ንተ የሶ​ር​ህያ ልጆች! ዛሬ ታስ​ቱኝ ዘንድ በእ​ኔና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ምን አለኝ? ዛሬስ ከእ​ስ​ራ​ኤል የሚ​ሞት አንድ ሰው የለም። ዛሬስ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ እንደ ነገ​ሥሁ አላ​ው​ቅ​ምን?”


ንጉ​ሡም ሳሚን፥ “አት​ሞ​ትም” አለው። ንጉ​ሡም ማለ​ለት።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች በጮኹ ጊዜ እርሱ ተነ​ሥቶ እጁ እስ​ከ​ሚ​ደ​ክ​ምና ከሰ​ይፉ ጋር እስ​ኪ​ጣ​በቅ ድረስ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን መታ፤ በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ መድ​ኀ​ኒት አደ​ረገ፤ ሕዝ​ቡም ከእ​ርሱ በኋላ የሞ​ቱ​ትን ለመ​ግ​ፈፍ ብቻ ተመ​ለሱ።


ሙሴም ለሕ​ዝቡ፥ “አት​ፍሩ፤ ዛሬ የም​ታ​ዩ​አ​ቸ​ውን ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አታ​ዩ​አ​ቸ​ው​ምና ቁሙ፤ ዛሬ ለእ​ና​ንተ የሚ​ያ​ደ​ር​ጋ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማዳን እዩ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚያ ቀን እስ​ራ​ኤ​ልን ከግ​ብ​ፃ​ው​ያን እጅ አዳ​ና​ቸው፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ግብ​ፃ​ው​ያን እንደ ሞቱ በባ​ሕር ዳር አዩ።


ሰውም እን​ደ​ሌለ አየ፤ የሚ​ረ​ዳም ሰው እን​ደ​ሌለ ተረዳ፤ ሰለ​ዚህ በክ​ንዱ ደገ​ፋ​ቸው፤ በይ​ቅ​ር​ታ​ውም አጸ​ና​ቸው።


ነገር ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ አሁን እኔ ባለ​ሁ​በት አለሁ፤ ለእ​ኔም የሰ​ጠኝ ጸጋው ለከ​ንቱ የሆ​ነ​ብኝ አይ​ደ​ለም፤ እኔም ከሁሉ ይልቅ ደከ​ምሁ፤ ነገር ግን በእኔ ላይ ያደ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ አጸ​ናኝ እንጂ እኔ አይ​ደ​ለ​ሁም።


ክፉ​ዎች ሰዎች ግን፥ “ያድ​ነን ዘንድ ይህ ሰው ማን ነው?” ብለው ናቁት፤ እጅ መን​ሻም አላ​መ​ጡ​ለ​ትም።


ሕዝ​ቡም ሳኦ​ልን፥ “በውኑ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ታላቅ መድ​ኀ​ኒት ያደ​ረገ ዮና​ታን ዛሬ ይሞ​ታ​ልን? ይህ አይ​ሁን፤ ዛሬ ለሕ​ዝቡ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር አድ​ር​ጎ​አ​ልና ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ከራሱ ጠጕር አን​ዲት በም​ድር ላይ አት​ወ​ድ​ቅም” አሉት። ሕዝ​ቡም ያን ጊዜ ስለ ዮና​ታን ጸለዩ፤ እር​ሱም አል​ተ​ገ​ደ​ለም።


ነፍ​ሱ​ንም በእጁ ጥሎ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ዉን ገደለ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ርሱ ታላቅ መድ​ኀ​ኒት አደ​ረገ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ አይ​ተው ደስ አላ​ቸው፤ በከ​ንቱ ዳዊ​ትን ትገ​ድ​ለው ዘንድ ስለ​ምን በን​ጹሕ ደም ላይ ትበ​ድ​ላ​ለህ?”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች