Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 10:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ‘እስ​ራ​ኤ​ልን ከግ​ብፅ አወ​ጣሁ፤ ከግ​ብፅ ንጉሥ ከፈ​ር​ዖ​ንም እጅ፥ ከሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​አ​ች​ሁም ነገ​ሥ​ታት ሁሉ እጅ አዳ​ን​ኋ​ችሁ’ አላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እንዲህ አላቸው፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እስራኤልን ከግብጽ አወጣሁት፤ ከግብጻውያን እጅ ይጨቍኗችሁ ከነበሩት ከሌሎቹ መንግሥታት ሁሉ እጅ ታደግኋችሁ።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 እንዲህ አላቸው፤ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፤ ‘እስራኤልን ከግብጽ አወጣሁት፤ ከግብፃውያን እጅ ይጨቁኗችሁ ከነበሩት ከሌሎቹ መንግሥታት ሁሉ እጅ ታደግኋችሁ።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እንዲህም አላቸው፦ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፦ ‘እናንተን እስራኤልን ከግብጽ አወጣኋችሁ፤ ከግብጽ ኀይልና ከሚጨቊኑአችሁ መንግሥታት ሁሉ ጭቈና አዳንኳችሁ’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 የእስራኤልንም ልጆች የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እስራኤልን ከግብጽ አወጣሁ፥ ከግብጻውያንም እጅ ከሚያስጨንቁአችሁም ነገሥታት ሁሉ እጅ አዳንኋችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 10:18
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በእ​ነ​ርሱ እጠራ ዘንድ፥ አም​ላ​ክም እሆ​ና​ቸው ዘንድ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ኋ​ቸው አም​ላ​ካ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።


በሚ​ገ​ፋ​ች​ሁም ጠላት ላይ በም​ድ​ራ​ችሁ ወደ ሰልፍ ስት​ወጡ በም​ል​ክት መለ​ከ​ቶ​ችን ንፉ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ፊት ትታ​ሰ​ባ​ላ​ችሁ፤ ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ትድ​ና​ላ​ችሁ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ከገ​ል​ገላ ወደ ቀላ​ው​ት​ም​ኖስ ወደ ቤቴል ወደ እስ​ራ​ኤል ቤት ወጥቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ከግ​ብፅ አው​ጥ​ቼ​አ​ች​ኋ​ለሁ፤ እሰ​ጣ​ች​ሁም ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ወደ ማል​ሁ​ላ​ቸው ምድር አግ​ብ​ቻ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔም፦ ከእ​ና​ንተ ጋር ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ቃል ኪዳን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አላ​ፈ​ር​ስም፤


ያዕ​ቆ​ብና ልጆቹ ወደ ግብጽ በገቡ ጊዜ ግብ​ጻ​ው​ያን አስ​ጨ​ነ​ቁ​አ​ቸው፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን ላከ፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም ከግ​ብጽ አው​ጥ​ተው በዚህ ቦታ አኖ​ሩ​አ​ቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች