Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 1:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ሐናም መልሳ እን​ዲህ አለ​ችው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ አይ​ደ​ለም፤ እኔስ ወራት የባ​ሳት ሴት ነኝ፤ ጠጅና ሌላ የሚ​ያ​ሰ​ክር ነገር አል​ጠ​ጣ​ሁም፤ ነገር ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ነፍ​ሴን አፈ​ሰ​ስሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ሐናም እንዲህ ብላ መለሰችለት፤ “ጌታዬ ሆይ፤ ሰክሬ አይደለም፤ እኔ ልቧ ክፉኛ የታወከባት ሴት ነኝ፤ ልቤን በእግዚአብሔር ፊት አፈሰስሁ እንጂ፣ የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አልጠጣሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ሐናም እንዲህ ብላ መለሰችለት፥ “ጌታዬ ሆይ፤ አይደለም፤ እኔስ ልቧ ክፉኛ ያዘነባት ሴት ነኝ፤ የልቤን ኀዘን በጌታ ፊት አፈሰስሁ እንጂ፥ የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አልጠጣሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እርስዋም እንዲህ ስትል መለሰችለት፦ “አይደለም ጌታዬ ሆይ! እኔ በጥልቅ ሐዘን ላይ ያለሁ ሰው ነኝ፤ ወይን ጠጅም ሆነ የሚያሰክር መጠጥ አልጠጣሁም፤ ነገር ግን ችግሬን ለእግዚአብሔር እያቀረብኩ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ሐናም፦ ጌታዬ ሆይ፥ አይደለም፥ እኔስ ልብዋ ያዘነባት ሴት ነኝ፥ ጠጅና ሌላ የሚያሰክር ነገር አልጠጣሁም፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ነፍሴን አፈሰስሁ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 1:15
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነፍሴ በኋ​ላህ ተከ​ታ​ተ​ለች፥ እኔ​ንም ቀኝህ ተቀ​በ​ለ​ችኝ።


ቆፍ። ተነሺ፤ በሌ​ሊት በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ሰዓት ጩኺ፥ በጌ​ታም ፊት ልብ​ሽን እንደ ውኃ አፍ​ስሺ፤ በጎ​ዳና ሁሉ ራስ ላይ በራብ ስለ ደከሙ ስለ ሕፃ​ና​ትሽ ነፍስ እጆ​ች​ሽን ወደ እርሱ አንሺ።


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ፥ ጐል​ማ​ስ​ነ​ቴ​ንም ደስ ወዳ​ሰ​ኛት ወደ አም​ላኬ እገ​ባ​ለሁ፤ አቤቱ፥ አም​ላኬ፥ በመ​ሰ​ንቆ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።


መብ​ረ​ቆ​ች​ህን ብልጭ አድ​ር​ጋ​ቸው፥ በት​ና​ቸ​ውም፤ ፍላ​ጾ​ች​ህን ላካ​ቸው፥ አስ​ደ​ን​ግ​ጣ​ቸ​ውም።


ቍጣ ጥበበኞችን ታጠፋለች፤ የለዘበ ቃል ቍጣን ይመልሳል፥ ሻካራ ቃል ግን ጠብን ያነሣሣል።


“አሁ​ንም ነፍሴ በው​ስጤ ፈሰ​ሰች፤ ጭን​ቀ​ትም በእኔ ላይ ሞላ፤


ኀዘ​ኔና ጭን​ቀቴ ስለ በዛ እስከ አሁን ድረስ እደ​ክ​ማ​ለ​ሁና ባር​ያ​ህን እንደ ኀጢ​አ​ተ​ኞች ሴቶች ልጆች አት​ቍ​ጠ​ራት።”


እነ​ር​ሱም ወደ መሴፋ ተሰ​በ​ሰቡ፤ ውኃም ቀድ​ተው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በም​ድር ላይ አፈ​ሰሱ፤ በዚ​ያም ቀን ጾሙ፤ በዚ​ያም፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በድ​ለ​ናል” አሉ። ሳሙ​ኤ​ልም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ በመ​ሴፋ ፈረደ።


እነ​ርሱ ግን ነፍ​ሴን ለከ​ንቱ ፈለ​ጓት፤ ወደ ምድር ጥልቅ ይግቡ።


የዐዋቂ ሰው ልብ ለሰውነቱ ኀዘን ነው፤ ደስ ባለውም ጊዜ ከጥል ጋር ግንኙነት የለውም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች