Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ነገሥት 7:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በታ​ላ​ቁም አደ​ባ​ባይ ዙሪያ የነ​በ​ረው ቅጥር እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እንደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ ቅጥ​ርና እንደ ቤቱ ወለል ሦስቱ ወገን በተ​ጠ​ረበ ድን​ጋይ አን​ዱም ወገን በዝ​ግባ ሳንቃ ተሠ​ርቶ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጠኛ አደባባይ ከመመላለሻ በረንዳው ጭምር እንደ ትልቁ አደባባይ አምሮ በተጠረበ ሦስት ረድፍ ድንጋይና ተስተካክሎ በተከረከመ በአንድ ረድፍ የዝግባ ሳንቃ የታጠረ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 የቤተ መንግሥቱ አደባባይ፥ የጌታ ቤት ውስጣዊ አደባባይና ወደ ቤተ መቅደሱ የሚያስገባው በር በእያንዳንዱ ባለ ሦስት ረድፍ የጥርብ ድንጋይ ሕንጻ ላይ አንዳንድ ረድፍ የሊባኖስ ዛፍ እንጨት ሠረገላ የተጋደመባቸው ግንቦች ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 የቤተ መንግሥቱ አደባባይ፥ የቤተ መቅደሱ ውስጣዊ አደባባይና ወደ ቤተ መቅደሱ የሚያስገባው በር በእያንዳንዱ ባለ ሦስት ረድፍ የጥርብ ድንጋይ ሕንጻ ላይ አንዳንድ ረድፍ የሊባኖስ ዛፍ እንጨት ሠረገላ የተጋደመባቸው ግንቦች ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 በታላቁም አደባባይ ዙሪያ የነበረው ቅጥር እንደ እግዚአብሔር ቤት እንደ ውስጠኛው አደባባይ ቅጥርና እንደ ቤቱ ወለል ሦስቱ ተራ በተጠረበ ድንጋይ አንዱም ተራ በዝግባ ሳንቃ ተሠርቶ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ነገሥት 7:12
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በመ​ቅ​ደ​ሱም ፊት ወለል ነበረ፤ ርዝ​መ​ቱም እንደ መቅ​ደሱ ወርድ ሃያ ክንድ፥ ወር​ዱም ከቤቱ ወደ ፊት ዐሥር ክንድ ነበረ፤ ቤቱ​ንም ሠርቶ ጨረሰ።


የው​ስ​ጠ​ኛ​ው​ንም አደ​ባ​ባይ ቅጥር ሦስ​ቱን ተራ በተ​ጠ​ረበ ድን​ጋይ፥ አን​ዱ​ንም ተራ በዝ​ግባ ሣንቃ ሠራው፤ በመ​ቅ​ደሱ ፊት ለፊት ላለው ቤት ወለ​ልም መጋ​ረጃ ሠራ።


በላ​ዩም ልክ ሆኖ የተ​ከ​ረ​ከመ ጥሩ ድን​ጋ​ይና የዝ​ግባ ሣንቃ ነበረ።


አዕ​ማ​ዱም ያሉ​በ​ትን ቤት ሠራ፤ ርዝ​መ​ቱም አምሳ ክንድ፥ ስፋ​ቱም ሠላሳ ክንድ ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ፊት ደግሞ ታላቅ አዕ​ማ​ድና መድ​ረክ ያሉ​በት ወለል ነበረ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በሁ​ለቱ ወለ​ሎች ላይ ለሰ​ማይ ሠራ​ዊት ሁሉ መሠ​ዊ​ያን ሠራ።


ደግ​ሞም የካ​ህ​ና​ቱን አደ​ባ​ባይ ፥ ታላ​ቁ​ንም አደ​ባ​ባይ፥ የአ​ደ​ባ​ባ​ዩ​ንም ደጆች ሠራ፤ ደጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም በናስ ለበጠ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በቤተ መቅ​ደስ በሰ​ሎ​ሞን ደጅ መመ​ላ​ለሻ ይመ​ላ​ለስ ነበር።


ጴጥ​ሮ​ስና ዮሐ​ን​ስም ይዘ​ውት ወደ መቅ​ደስ ሲገቡ ሕዝቡ ሁሉ ደን​ግ​ጠው ወደ ሰሎ​ሞን መመ​ላ​ለሻ ወደ እነ​ርሱ ሮጡ።


በሐ​ዋ​ር​ያት እጅም በሕ​ዝቡ ዘንድ ተአ​ም​ራ​ትና ድንቅ ሥራ​ዎች ይሠሩ ነበር፤ በቤተ መቅ​ደ​ስም በሰ​ሎ​ሞን መመ​ላ​ለሻ በአ​ን​ድ​ነት ነበሩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች