Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ቆሮንቶስ 11:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ አመ​ሰ​ግ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ ዘወ​ትር ታስ​ቡ​ኛ​ላ​ች​ሁና፤ ያስ​ተ​ማ​ር​ኋ​ች​ሁ​ንም ትም​ህ​ርት ጠብ​ቃ​ች​ኋ​ልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 በሁሉም ነገር ስለምታስቡልኝና ከእኔ የተቀበላችሁትን ትምህርት አጥብቃችሁ ስለ ያዛችሁ አመሰግናችኋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ወንድሞች ሆይ! በሁሉ ስለምታስቡኝና እኔ ያስተላለፍኩላችሁን ትውፊት አጥብቃችሁ ስለ ያዛችሁ አመሰግናችኋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ዘወትር ስለምታስታውሱኝና የሰጠኋችሁንም ትውፊት አጥብቃችሁ ስለ ያዛችሁ፥ አመሰግናችኋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ወንድሞች ሆይ፥ በሁሉ ስለምታስቡኝና አሳልፌ እንደ ሰጠኋችሁ ወግን ፈጽማችሁ ስለ ያዛችሁ አመሰግናችኋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ቆሮንቶስ 11:2
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሁለ​ቱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ጻድ​ቃን ነበሩ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥር​ዐ​ትና በት​እ​ዛ​ዙም ሁሉ ያለ ነውር የሚ​ሄዱ ነበሩ።


ይህ​ንም የነ​ገ​ር​ኋ​ችሁ ላመ​ሰ​ግ​ና​ችሁ አይ​ደ​ለም፤ በም​ት​ሰ​በ​ሰ​ቡ​በት ጊዜ ወደ ዝቅ​ተኛ እንጂ ወደ​ሚ​ሻል ግብር አት​ሄ​ዱ​ምና።


በውኑ የም​ት​በ​ሉ​በ​ትና የም​ት​ጠ​ጡ​በት ቤት የላ​ች​ሁ​ምን? ወይስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ታስ​ነ​ቅ​ፋ​ላ​ች​ሁን? ነዳ​ያ​ን​ንስ ታሳ​ፍ​ሩ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ች​ሁን? ምን እላ​ለሁ? በዚህ አመ​ሰ​ግ​ና​ች​ኋ​ለ​ሁን? አላ​መ​ሰ​ግ​ና​ች​ሁም።


ያስ​ተ​ማ​ር​ኋ​ች​ሁን ታስቡ እንደ ሆነ በቃሌ አስ​ተ​ም​ሬ​አ​ች​ኋ​ለሁ፤ ያለ​ዚያ ግን ማመ​ና​ችሁ ከንቱ ነው።


ስለ​ዚ​ህም በየ​ስ​ፍ​ራው በአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ሁሉ እን​ዳ​ስ​ተ​ማ​ርሁ በክ​ር​ስ​ቶስ ኢየ​ሱስ የሄ​ድ​ሁ​በ​ትን መን​ገድ ይገ​ል​ጥ​ላ​ችሁ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የታ​መ​ነና ልጄ ወዳጄ የሆነ ጢሞ​ቴ​ዎ​ስን ልኬ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


ነገር ግን ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አደ​ለው፥ ሁሉም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ጠራው እን​ዲሁ ይኑር፤ ለአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ና​ትም ሁሉ እን​ዲህ ሥር​ዐት እን​ሠ​ራ​ለን።


ደግሞ እናንተ ቃሉን በብዙ መከራ ከመንፈስ ቅዱስ ደስታ ጋር ተቀብላችሁ፥ እኛንና ጌታን የምትመስሉ ሆናችሁ፤


አሁን ግን ጢሞቴዎስ ከእናንተ ዘንድ ወደ እኛ መጥቶ ስለ እምነታችሁና ስለ ፍቅራችሁ የምሥራች ብሎ በነገረን ጊዜ፥ እኛም እናያችሁ ዘንድ እንደምንናፍቅ ታዩን ዘንድ እየናፈቃችሁ ሁልጊዜ በመልካም እንደምታስቡን በነገረን ጊዜ፥


እንግዲያስ ወንድሞች ሆይ! ጸንታችሁ ቁሙ፤ በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ወግ ያዙ።


ወንድሞች ሆይ! ከእኛ እንደ ተቀበለው ወግ ሳይሆን ያለ ሥርዐት ከሚሄድ ወንድም ሁሉ ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች