Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 8:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ከዚያም ኢያሱ ሰዎቹን ላካቸው፤ እነርሱም ሄደው ከጋይ በስተምዕራብ በቤቴልና በጋይ መካከል ባለው ቦታ አደፈጡ፤ ኢያሱ ግን እዚያው ከሕዝቡ ጋራ ዐደረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ኢያሱም ሰደዳቸው፤ ወደሚደበቁበትም ስፍራ ሄዱ፥ በጋይና በቤቴል መካከልም በጋይ በምዕራብ በኩል ተቀመጡ፤ ኢያሱ ግን በዚያች ሌሊት በሕዝቡ መካከል አደረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ከዚህ በኋላ ኢያሱ ወታደሮቹን ላከ፤ ከዐይ በስተምዕራብ በኩል በዐይና በቤትኤል መካከል ድብቅ ጦር ሆነው ቈዩ፤ ኢያሱም በሠራዊቱ መካከል ዐደረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ኢያ​ሱም ላካ​ቸው፤ ወደ​ሚ​ደ​በ​ቁ​በ​ትም ስፍራ ሄዱ፤ በጋ​ይና በቤ​ቴል መካ​ከ​ልም በጋይ በባ​ሕር በኩል ተቀ​መጡ፤ ኢያሱ ግን በዚ​ያች ሌሊት በሕ​ዝቡ መካ​ከል አደረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ኢያሱም ሰደዳቸው፥ ወደሚደበቁበትም ስፍራ ሄዱ፥ በጋይና በቤቴል መካከልም በጋይ በምዕራብ በኩል ተቀመጡ፥ ኢያሱ ግን በዚያች ሌሊት በሕዝቡ መካከል አደረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 8:9
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚያም ተነሥቶ ከቤቴል በስተምሥራቅ ወዳሉት ተራሮች ሄደ፤ ቤቴልን በምዕራብ፣ ጋይን በምሥራቅ አድርጎ ድንኳን ተከለ፣ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ የእግዚአብሔርን ስም ጠርቶ ጸለየ።


ስለዚህ የያዕቆብ እጅ መንሻ ከርሱ አስቀድሞ ተላከ፤ እርሱ ራሱ ግን እዚያው በሰፈሩበት ቦታ ዐደረ።


የቤቴልና የጋይ ሰዎች 223


የቤቴልና የጋይ ሰዎች 123


ኢያሱ ከቤቴል በስተምሥራቅ ካለችው ከቤትአዌን አጠገብ ወደምትገኘው ወደ ጋይ ከኢያሪኮ ሰዎችን ልኮ፣ “ወደዚያ ውጡ፤ አገሪቱንም ሰልሉ” አላቸው፤ ሰዎቹም ወጥተው ጋይን ሰለሉ።


በማግስቱም ጧት ኢያሱ ማልዶ በመነሣት ወንዶቹን ሰበሰበ፤ እርሱና የእስራኤል አለቆችም ከፊት ሆነው እየመሯቸው ወደ ጋይ ወጡ።


ኢያሱ ቀደም ብሎ ዐምስት ሺሕ ሰው ያህል በመውሰድ ከከተማዪቱ በስተምዕራብ፣ በቤቴልና በጋይ መካከል እንዲያደፍጡ አድርጎ ነበር።


ከተማዪቱን ስትይዙም በእሳት አቃጥሏት፤ እግዚአብሔር ያዘዘውንም አድርጉ፤ እነሆ አዝዣችኋለሁ።”


ይህንም፣ በቤቴል፣ በደቡብ ራሞትና በየቲር ለነበሩ፣


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች