Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 8:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 የጋይ ሰዎች ወደ ኋላ ዞረው ሲመለከቱ የከተማዪቱ ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ፤ ወደ ምድረ በዳ ይሸሹ የነበሩት እስራኤላውያን ፊታቸውን ስላዞሩባቸውም፣ በየትኛውም በኩል ማምለጫ መንገድ አልነበራቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 የጋይም ሰዎች ወደ ኋላቸው ዞረው የከተማይቱ ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ፤ ወደ ምድረ በዳም የሸሸው ሕዝብ በሚያሳድዱአቸው ላይ ስለ ተመለሱ ወዲህና ወዲያም መሸሽ አልቻሉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 የዐይ ከተማ ሰዎችም ወደ ኋላ መለስ ብለው ባዩ ጊዜ የከተማይቱ ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ፤ ወደ ምድረ በዳ የሸሹት እስራኤላውያን በአሳዳጆቻቸው ላይ ስለ ተመለሱባቸው፥ በየትም በኩል ለማምለጥ አልቻሉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 የጋ​ይም ሰዎች ወደ ኋላ​ቸው ዞረው በተ​መ​ለ​ከቱ ጊዜ የከ​ተ​ማ​ዪቱ ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ፤ ወዲ​ህና ወዲያ መሸሽ አል​ቻ​ሉም፤ ወደ ምድረ በዳም የሸሹ ሕዝብ በሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​አ​ቸው ላይ ተመ​ለሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 የጋይም ሰዎች ወደ ኋላቸው ዞረው የከተማይቱ ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ፥ ወዲህና ወዲያም መሸሽ አልቻሉም፥ ወደ ምድረ በዳም የሸሹ ሕዝብ በሚያሳድዱአቸው ላይ ተመለሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 8:20
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ደግሞም እንዲህ አሉ፤ “ሃሌ ሉያ! ጢስ ከርሷ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይወጣል።”


“ከርሷ ጋራ ያመነዘሩና በምቾት የኖሩ የምድር ነገሥታት፣ እርሷ ስትቃጠል የሚወጣውን ጢስ ሲያዩ ስለ እርሷ ያለቅሳሉ፤ ያዝናሉም።


እሳቷ ሌሊትና ቀን አይጠፋም፤ ጢሷም ለዘላለም ይትጐለጐላል፤ ከትውልድ እስከ ትውልድ ባድማ ትሆናለች፤ ማንም በዚያ ዳግም አያልፍም።


ልበ ሙሉ የሆኑት ተዘርፈዋል፤ አንቀላፍተውም ተኝተዋል፤ ከኀያላኑም መካከል፣ እጁን ማንቀሳቀስ የቻለ የለም።


የክፉዎች ዐይን ግን ትጨልማለች፤ ማምለጫም አያገኙም፤ ተስፋቸውም ሞት ብቻ ነው።”


ሰዶምንና ገሞራን፣ እንዲሁም በረባዳው ስፍራ የሚገኘውን ምድር ሁሉ ቍልቍል ተመለከተ፤ ከእቶን የሚወጣ የመሰለ ጥቅጥቅ ያለ ጢስ ከምድሪቱ ወደ ላይ ሲትጐለጐል አየ።


ይህን እንዳደረገም ያደፈጡት ሰዎች ከተደበቁበት ስፍራ በፍጥነት ወጥተው ወደ ፊት ሮጡ፤ ገብተው ከተማዪቱን ያዟት፤ ወዲያውኑም በእሳት አቃጠሏት።


ኢያሱና እስራኤል ሁሉ ያደፈጠው ጦር ከተማዪቱን መያዙንና ጢሱ ወደ ላይ መውጣቱን ሲያዩ፣ ወደ ኋላ ተመልሰው በጋይ ሰዎች ላይ አደጋ ጣሉባቸው፤


የእስራኤል ሰዎች ያሸመቀው ጦር በከተማዪቱ ውስጥ ከባድ የጢስ ደመና ምልክት እንዲያሳይ፣


ነገር ግን የጢሱ ዐምድ ከከተማዪቱ መነሣት በጀመረ ጊዜ፣ ብንያማውያን ወደ ኋላቸው ዞረው የመላዪቱ ከተማ ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ።


ከዚያም እስራኤላውያን ዞረው አጠቋቸው፤ በዚህ ጊዜ ብንያማውያን ጥፋት እንደ ደረሰባቸው ስላወቁ እጅግ ደነገጡ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች