| ኢያሱ 3:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም1 ኢያሱም ማልዶ ተነሣ። ከእስራኤላውያንም ሁሉ ጋራ ከሰጢም ወደ ዮርዳኖስ መጥተው ወንዙን ከመሻገራቸው በፊት በዚያ ሰፈሩ።ምዕራፉን ተመልከት መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 በማግስቱም ኢያሱ ማልዶ ተነሣ፥ እርሱና የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ከሰጢም ተነሥተው ወደ ዮርዳኖስ መጡ፤ ሳይሻገሩም በዚያ አደሩ።ምዕራፉን ተመልከት አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 በማግስቱ ኢያሱና የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ማልደው ተነሡ፤ የሺጢምን ሰፈር ለቀው ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ሄዱ፤ ከመሻገራቸውም በፊት በዚያ ሰፈሩ፤ምዕራፉን ተመልከት የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 ኢያሱም ማልዶ ተነሣ፤ እርሱና እስራኤልም ሁሉ ከሰጢም ተጕዘው ወደ ዮርዳኖስ መጡ፤ ሳይሻገሩም በዚያ አደሩ።ምዕራፉን ተመልከት መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 ኢያሱም ማልዶ ተነሣ፥ እርሱና የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ከሰጢም ተነሥተው ወደ ዮርዳኖስ መጡ፥ ሳይሻገሩም በዚያ አደሩ።ምዕራፉን ተመልከት |