Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 21:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ስለዚህ እስራኤላውያን እግዚአብሔር በሙሴ በኩል ባዘዘው መሠረት፣ እነዚህን ከተሞችና መሰማሪያቸውን ለሌዋውያኑ በዕጣ መደቡላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ጌታም በሙሴ አማካይነት እንዳዘዘ የእስራኤል ልጆች እነዚህን ከተሞችና መሰማሪያቸውን ለሌዋውያን በዕጣ ሰጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 በሙሴ አማካይነት እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት የእስራኤል ሕዝብ እነዚህን ከተሞችና የግጦሽ ምድር ለሌዋውያን በዕጣ አካፈሉአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እነ​ዚ​ህን ከተ​ሞ​ችና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ለሌ​ዋ​ው​ያን በዕጣ ሰጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እግዚአብሔርም በሙሴ እጅ እንዳዘዘ የእስራኤል ልጆች እነዚህን ከተሞችና መሰምርያቸውን ለሌዋውያን በዕጣ ሰጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 21:8
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለዚህ እስራኤላውያን ከወረሱት ምድር ላይ የሚከተሉትን ከተሞችና መሰማሪያዎች እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ለሌዋውያኑ ሰጡ።


ዕጣ መጣጣል ሙግትን ያስቆማል፤ ኀይለኛ ባላንጣዎችንም ይገላግላል።


ዕጣ በጕያ ውስጥ ይጣላል፤ ውሳኔው በሙሉ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።


የሰባቱን የመሬት ክፍፍል ዝርዝር መግለጫ ጽፋችሁ ወደ እኔ ታመጡና በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት ዕጣ እጥልላችኋለሁ።


ከተሞቹ ለእነርሱ መኖሪያ፣ የግጦሽ መሬቱ ለከብቶቻቸው፣ ለበግና ለፍየል መንጎቻቸውና ለሌሎቹም እንስሶቻቸው ይሆናሉ።


ምድሪቱንም በየጐሣዎቻችሁ በዕጣ ተከፋፈሉ። ከፍ ያለ ቍጥር ላለው ሰፋ ያለውን፣ ዝቅተኛ ቍጥር ላለው ደግሞ አነስተኛውን ስጡ፤ ምንም ይሁን ምን በዕጣ የወጣላቸው፣ የየራሳቸው ርስት ይሆናል። አከፋፈሉም በየአባቶቻችሁ ነገዶች አንጻር ይሁን።


ስለዚህ የሮቤልና የጋድ ሰዎች ወደ ሙሴ፣ ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛርና ወደ ማኅበረ ሰቡ መሪዎች መጥተው እንዲህ አሉ፤


“ስምዖንና ሌዊ ወንድማማቾች፣ ሰይፎቻቸው የዐመፅ መሣሪያዎች ናቸው።


ለሜራሪ ዝርያዎች በየጐሣቸው ከሮቤል፣ ከጋድና ከዛብሎን ነገዶች ዐሥር ከተሞች ተመደቡላቸው።


ከይሁዳና ከስምዖን ነገዶች ደግሞ ከዚህ በታች በስም የተጠቀሱትን ከተሞች በዕጣ መደቡላቸው።


እጅግ አስፈሪ የሆነ ቍጣቸው፣ ጭከና የተሞላ ንዴታቸው የተረገመ ይሁን፤ በያዕቆብ እበትናቸዋለሁ፤ በመላው እስራኤልም አሠራጫቸዋለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች