Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 21:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 የመጀመሪያው ዕጣ ለቀዓት ዘሮች በየጐሣቸው ወጣ፤ የካህኑ የአሮን ዝርያዎች ለሆኑት ሌዋውያን ከይሁዳ፣ ከስምዖንና ከብንያም ነገዶች ዐሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ተመደቡላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ለቀዓትም ወገኖች ዕጣ ወጣ፤ ሌዋውያንም ለነበሩ ለካህኑ ለአሮን ልጆች ከይሁዳ ነገድ፥ ከስምዖንም ነገድ፥ ከብንያምም ነገድ ዐሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ወሰዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 የመጀመሪያው ዕጣ ለቀዓት ጐሣ ወጣ፤ ከሌዊ ነገድ ለካህኑ ለአሮን ልጆች ዐሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ተከፋፈለ፤ እነዚህም ከተሞች የተወሰዱት ከይሁዳ፥ ከስምዖንና ከብንያም ነገዶች ይዞታዎች ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ለቀ​ዓ​ትም ወገ​ኖች ልጆች ዕጣ ወጣ፤ ሌዋ​ው​ያ​ንም ለነ​በሩ ለካ​ህኑ ለአ​ሮን ልጆች ከይ​ሁዳ ነገድ፥ ከስ​ም​ዖ​ንም ነገድ፥ ከብ​ን​ያ​ምም ነገድ ዐሥራ ሦስት ከተ​ሞች በዕጣ ተሰ​ጡ​አ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ለቀዓትም ወገኖች ዕጣ ወጣ፥ ሌዋውያንም ለነበሩ ለካህኑ ለአሮን ልጆች ከይሁዳ ነገድ፥ ከስምዖንም ነገድ፥ ከብንያምም ነገድ አሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ሆኑላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 21:4
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንዲሁም የአሮን ልጅ አልዓዛር ሞተ፤ እርሱም በኰረብታማው በኤፍሬም አገር በሚገኘው ለልጁ ለፊንሐስ በዕጣ በደረሰው በጊብዓ ምድር ተቀበረ።


የእንበረማውያን፣ የይስዓራውያን፣ የኬብሮናውያንና የዑዝኤላውያን ጐሣዎች ከቀዓት ወገን ናቸው፤ እነዚህ የቀዓት ጐሣዎች ነበሩ።


ስለዚህ እስራኤላውያን ከወረሱት ምድር ላይ የሚከተሉትን ከተሞችና መሰማሪያዎች እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ለሌዋውያኑ ሰጡ።


ለቀሩት ለቀዓት ዘሮች ደግሞ ከኤፍሬምና ከዳን ነገድ ጐሣዎች፣ እንዲሁም ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ጐሣዎች ዐሥር ከተሞች በዕጣ ተመደቡላቸው።


በትውልዳቸው መሠረት የሌዊ ወንዶች ልጆች ስሞች እነዚህ ነበሩ፤ ጌርሶን፣ ቀዓትና ሜራሪ ናቸው። ሌዊ መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ኖረ።


እንበረም የአጎቱን እናት ዮካብድን አገባ፤ እርሷም አሮንና ሙሴን ወለደችለት። እንበረም መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ኖረ።


እንዲሁም የሔማን ወንድም አሳፍ በስተ ቀኙ ሆኖ ያገለግል ነበር፤ አሳፍ የበራክያ ልጅ፣ የሳምዓ ልጅ፣


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች