Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 20:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ስለዚህም በኰረብታማው በንፍታሌም ምድር በገሊላ ቃዴስን፣ በኰረብታማው በኤፍሬም ምድር ሴኬምን፣ በኰረብታማው በይሁዳ ምድር ኬብሮን የምትባለውን ቂርያት አርባቅን ለዩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 በንፍታሌም ባለው በተራራማው አገር በገሊላ ቃዴስን፥ በኤፍሬምም ባለው በተራራማው አገር ሴኬምን፥ በይሁዳም ባለው በተራራማው አገር ኬብሮን የምትባለውን ቂርያት-አርባቅን ለዩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ስለዚህም የንፍታሌም ይዞታ በሆነችው በኮረብታማዋ ምድር በምትገኘው በገሊላ፥ ቄዴሽ ተብላ የምትጠራውን፥ በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ሴኬምንና በኮረብታማው በይሁዳ ምድር ኬብሮን የምትባለው ቂርያት አርባቅን መርጠው ለዩ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 በን​ፍ​ታ​ሌም ባለው በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር በገ​ሊላ ቃዴ​ስን፥ በኤ​ፍ​ሬ​ምም ባለው በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ሴኬ​ምን፥ በይ​ሁ​ዳም ባለው በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ኬብ​ሮን የም​ት​ባ​ለ​ውን የአ​ር​ቦ​ቅን ከተማ ለዩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 በንፍታሌም ባለው በተራራማው አገር በገሊላ ቃዴስን፥ በኤፍሬምም ባለው በተራራማው አገር ሴኬምን፥ በይሁዳም ባለው በተራራማው አገር ኬብሮን የምትባለውን ቂርያትአርባቅን ለዩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 20:7
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነርሱም በተራራማው የይሁዳ ምድር ያለችውን ኬብሮን የተባለችውን ቂርያት አርባቅን በዙሪያዋ ካለው መሰማሪያ ጋራ ሰጧቸው፤ አርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ።


ማርያምም በዚያው ሰሞን በፍጥነት ተነሥታ ወደ ደጋው አገር፣ ወደ አንድ የይሁዳ ከተማ ሄደች፤


ከንፍታሌም ነገድ በገሊላ የሚገኘውን ቃዴስን፣ ሐሞንንና፣ ቂርያታይምን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ።


ከንፍታሌም ነገድ፣ በገሊላ ውስጥ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ የሆነችው ከተማ ቃዴስ፣ ሐሞትዶርና ቀርታን እነዚህ ሦስት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፤


በተራራማው በኤፍሬም አገርም ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ የሆነችው ሴኬምና ጌዝር፣


እንደዚሁም ለነፍሰ ገዳይ የመማፀኛ ከተማ የሆነችውን ኬብሮንንና ልብናን ከነመሰማሪያቸው ለካህኑ ለአሮን ልጆች ሰጧቸው፤


ኬብሮን ቀድሞ ከዔናቃውያን ሁሉ ታላቅ በሆነው ሰው በአርባቅ ስም ቂርያት አርባቅ ተብላ ትጠራ ነበር። ከዚያም ምድሪቱ ከጦርነት ዐረፈች።


እስራኤላውያን ሁሉ ሊያነግሡት ወደ ሴኬም መጥተው ስለ ነበር፣ ሮብዓም ወደ ሴኬም ሄደ።


በከነዓን ምድር፣ በቂርያት አርባቅ ማለትም በኬብሮን ከተማ ሞተች፤ አብርሃምም ለሣራ ሊያለቅስና ሊያዝን መጣ።


“ለሌዋውያኑ ከምትሰጧቸው ከተሞች ስድስቱ፣ ሰው የገደለ ሸሽቶ የሚጠጋባቸው መማፀኛ ከተሞች ይሆናሉ፤ በተጨማሪም አርባ ሁለት ከተሞች ስጧቸው፤


በዚያ ጊዜ ሙሴ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ሦስት ከተሞችን ለየ፤


አምላክህን እግዚአብሔርን እንድትወድድና ምን ጊዜም በመንገዱ እንድትሄድ ዛሬ የማዝዝህን እነዚህን ሕግጋት ሁሉ በጥንቃቄ የምትጠብቅ ከሆነ፣ በእነዚህ ላይ ሌሎች ሦስት ከተሞችን ትጨምራለህ።


የቃዴስ ንጉሥ፣ አንድ በቀርሜሎስ የሚገኘው የዮቅንዓም ንጉሥ፣ አንድ


እንደዚሁም ከዮርዳኖስ ማዶ ከኢያሪኮ በስተምሥራቅ በሮቤል ነገድ ይዞታ ውስጥ ከፍታ ባለው ምድረ በዳ ያለችውን ቦሶርን፣ በጋድ ነገድ ይዞታ ውስጥ ባለችው በገለዓድ የምትገኘውን ራሞትንና በምናሴ ነገድ ይዞታ ውስጥ በባሳን የምትገኘውን ጎላንን ለዩ።


ኢያሱ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት፣ ከይሁዳ ድርሻ ላይ ከፍሎ ኬብሮን የተባለችውን ቂርያት አርባቅን ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ሰጠው፤ አርባቅም የዔናቅ አባት ነበረ።


የተመሸጉትም ከተሞች እነዚህ ናቸው፤ ጺዲም፣ ጼር፣ ሐማት፣ ረቃት፣ ኬኔሬት፣


አዳማ፣ ራማ፣ አሦር፣


ቃዴስ፣ ኤድራይ፣ ዓይንሐጾር፣


ከዚያም ኢያሱ የእስራኤልን ነገዶች ሁሉ በሴኬም ሰበሰበ፤ የእስራኤልንም ሽማግሌዎች፣ መሪዎች፣ ፈራጆችና ሹማምት ጠራ፤ እነርሱም በእግዚአብሔር ፊት ቆሙ።


የይሩባኣል ልጅ አቢሜሌክ ወደ እናቱ ወንድሞች ወደ ሴኬም ሄደ። እነርሱንና የእናቱን ጐሣዎች በሙሉ እንዲህ አላቸው፤


እስራኤላውያን ሁሉ ሊያነግሡት ወደ ሴኬም መጥተው ስለ ነበር፣ ሮብዓም ወደ ሴኬም ሄደ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች