Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 14:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እነሆ ቤተ ዘመዱ ሁሉ በባሪያህ ላይ ተነሥተው፣ ‘ወንድሙን ስለ ገደለ እንገድለዋለንና ወንድሙን የገደለውን ሰው አሳልፈሽ ስጪን፣ ከዚያም ወራሽ አልባ ትሆኛለሽ’ ይሉኛል፤ ስለዚህ የቀረኝን አንዱን መብራቴን አጥፍተው፣ ባሌን በምድር ላይ ያለ ስምና ያለ ዘር ሊያስቀሩት ነው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እነሆ ዘመዶቼ ሁሉ በአገልጋይህ ላይ ተነሥተው፥ ‘ወንድሙን የገደለውን ሰው አሳልፈሽ ስጪን፥ ወራሽ እንኳ ብናጠፋ ወንድሙን ስለ ገደለ እንገድለዋለን’ ይሉኛል፤ ስለዚህ የቀረኝን አንዱን መብራቴን በማጥፋት፥ ባሌን በምድር ላይ ያለ ስምና ያለ ዘር ሊያስቀሩት ነው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ንጉሥ ሆይ! እነሆ አሁን ዘመዶቼ ሁሉ በእኔ በአገልጋይህ ላይ ተነሥተው ‘ወንድሙን ስለ ገደለ ወራሽ እንኳ ብናጠፋ እንገድለው ዘንድ ወንድሙን የገደለውን ሰው ስጪን’ እያሉ አስቸገሩኝ። ታዲያ፥ እንዲህ የሚያደርጉ ከሆነ የቀረኝን አንድ ተስፋ ሊያጠፉብኝና በምድርም ላይ የባሌን ስምና ዘር ሊያሳጡ ነው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እነ​ሆም፥ ዘመ​ዶች ሁሉ በባ​ሪ​ያህ ላይ ተነሡ፤ ስለ ገደ​ለው ስለ ወን​ድሙ ነፍስ እን​ገ​ድ​ለው ዘንድ ወን​ድ​ሙን የገ​ደ​ለ​ውን አውጪ አሉኝ፤ እን​ዲ​ሁም ደግሞ ለባሌ ስምና ዘር በም​ድር ላይ እን​ዳ​ይ​ቀር ወራ​ሹን የቀ​ረ​ውን መብ​ራ​ቴን ያጠ​ፋሉ፤”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እነሆም፥ ዘመዶች ሁሉ በባሪያህ ላይ ተነሥተው፦ ስለ ገደለው ስለ ወንድሙ ነፍስ እንገድለው ዘንድ ወንድሙን የገደለውን አውጪ አሉኝ፥ እንዲሁም ደግሞ ወራሹን የቀረውን መብራቴን ያጠፋሉ፥ የባሌን ስምና ዘርም ከምድር ላይ አያስቀሩም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 14:7
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን ቍጣው በርዶለት ያደረግህበትን ከረሳ በኋላ፣ እንድትመለስ እልክብህና ትመጣለህ። ሁለታችሁንም በአንድ ቀን ለምን ልጣ?”


እነሆ፤ ዛሬ ከምድሪቱ አባረርኸኝ፤ ከፊትህም እሸሸጋለሁ፤ በምድር ላይ ኰብላይና ተንከራታች እሆናለሁ፤ የሚያገኘኝም ሁሉ ይገድለኛል።”


የቤተ ሰቡ ሰው፣ ሽማግሌዎችም ከመሬት ሊያስነሡት በአጠገቡ ቆሙ፤ እርሱ ግን እንቢ አለ፤ ዐብሯቸውም አንዳች ነገር አልበላም።


እኔ አገልጋይህ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩኝ፤ ሜዳ ላይ እርስ በርሳቸው ተጣሉ፤ ገላጋይም ስላልነበረ፣ አንዱ ሌላውን መትቶ ገደለው።


ንጉሡም ሴቲቱን፣ “አንቺ ወደ ቤትሽ ሂጂ፤ ስለ ጕዳይሽ አስፈላጊውን ትእዛዝ እሰጣለሁ” አላት።


ደም መላሹም ነፍሰ ገዳዩን ይግደለው፤ ባገኘውም ጊዜ ይግደለው።


“ነገር ግን ገበሬዎቹ ልጁን ባዩት ጊዜ፣ ‘ይህማ ወራሹ ነው፤ ኑ፣ እንግደለውና ርስቱን እንውረስ’ ተባባሉ።


በመጀመሪያ የምትወልደውም ልጅ ስሙ ከእስራኤል ፈጽሞ እንዳይጠፋ በሟች ወንድሙ ስም ይጠራ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች