Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 1:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 “ከሞቱት ሰዎች ደም፣ ከኀያላኑም ሥብ፣ የዮናታን ቀስት ተመልሳ አልመጣችም፤ የሳኦልም ሰይፍ በከንቱ አልተመለሰችም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ከሞቱት ሰዎች ደም፥ ከኀያላኑም ሥብ፥ የዮናታን ቀስት ተመልሳ አልመጣችም፤ የሳኦልም ሰይፍ በከንቱ አልተመለሰችም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 የዮናታን ቀስት ሳይገድል የማይመለስ፥ የሳኦልም ሰይፍ ጠላትን የሚቈራርጥ ኀያላንን መትቶ የሚሰብር፥ ጠላትን የሚገድል ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ከሞ​ቱት ደምና ከኀ​ያ​ላን ስብ፥ የዮ​ና​ታን ቀስት ባዶ​ዋን አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ የሳ​ኦ​ልም ሰይፍ ባዶ​ዋን አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ከሞቱት ደምና ከኃያላን ስብ የዮናታን ቀስት አልተመለሰችም፥ የሳኦልም ሰይፍ በከንቱ አልተመለሰም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 1:22
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የታላላቅ መንግሥታትን ማኅበር፣ ከሰሜን በባቢሎን ላይ አስነሣለሁ፤ እነርሱም በርሷ ላይ ይሰለፋሉ፤ መጥተውም ይይዟታል። ቀስቶቻቸው ባዶ እጃቸውን እንደማይመለሱ፣ እንደ ሥልጡን ተዋጊዎች ናቸው።


ሰይፌ ሥጋ በሚበላበት ጊዜ፣ ፍላጾቼ በደም እንዲሰክሩ አደርጋለሁ፤ ደሙ የታረዱትና የምርኮኞች፣ የጠላት አለቆችም ራስ ደም ነው።”


ሳኦል በእስራኤል ላይ በትረ መንግሥቱን ከጨበጠ በኋላ፣ በዙሪያው ያሉትን ጠላቶቹን ማለትም ሞዓብን፣ አሞናውያንን፣ ኤዶምን፣ የሱባን ነገሥታትና ፍልስጥኤማውያንን ወጋቸው። በሄደበት ሁሉ ድል ይነሣ ነበር።


በጀግንነት ተዋግቶ አማሌቃውያንን አሸነፈ፤ እስራኤልንም ይዘርፏቸው ከነበሩት እጅ ታደጋቸው።


ዮናታን የለበሰውን ካባ አውልቆ ከነጦር ልብሱ፣ በተጨማሪም ሰይፉን፣ ቀስቱንና መታጠቂያውን ሰጠው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች