Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 13:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 በዚህ ጊዜ ሳኦል፣ “የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕቱን አምጡልኝ” አለ። ከዚያም የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀረበ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 በዚህ ጊዜ ሳኦል፥ “የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነት መሥዋዕቱን አምጡልኝ” አለ። ከዚያም የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀረበ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ስለዚህም ሳኦል ሕዝቡን “የሚቃጠለውንና ለደኅንነት የሚሆነውን የአንድነት መሥዋዕት አምጡልኝ” ብሎ በማዘዝ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀረበ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ሳኦ​ልም፥ “የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት አም​ጡ​ልኝ” አለ። የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት አሳ​ረገ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ሳኦልም፦ የሚቃጠል መሥዋዕትና የደኅንነት መሥዋዕት አምጡልኝ አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 13:9
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊትም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት አቀረበ። ከዚያም እግዚአብሔር ስለ ምድሪቱ የቀረበውን ጸሎት ሰማ፤ በእስራኤል ላይ የመጣውም መቅሠፍት ቆመ።


ከሁሉ የሚበልጠው የማምለኪያ ኰረብታ ገባዖን ስለ ነበረ፣ ንጉሡ መሥዋዕት ለማቅረብ ወደዚያ ሄደ። ሰሎሞን በዚያ መሠዊያ ላይ አንድ ሺሕ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ።


በእግዚአብሔር ፊት ጸጥ በል፤ በትዕግሥትም ተጠባበቀው፤ መንገዱ በተቃናለት፣ ክፋትንም በሚሸርብ ሰው ልብህ አይሸበር።


እግዚአብሔር የክፉዎችን መሥዋዕት ይጸየፋል፤ የቅኖች ጸሎት ግን ደስ ያሠኘዋል።


“ለደረሰብኝ በደል ብድሬን ባልመልስ!” አትበል፤ እግዚአብሔርን ጠብቅ፤ እርሱ ይታደግሃል።


የክፉ ሰው መሥዋዕት አስጸያፊ ነው፤ በክፉ ዐላማ ሲያቀርብማ የቱን ያህል አስከፊ ይሆን!


ከመሥዋዕት ይልቅ ጽድቅንና ፍትሕን ማድረግ፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት አለው።


ነገር ግን ወይፈን የሚሠዋልኝ፣ ሰው እንደሚገድል ነው፤ የበግ ጠቦት የሚያቀርብልኝ፣ የውሻ ዐንገት እንደሚሰብር ሰው ነው፤ የእህል ቍርባን የሚያዘጋጅልኝ፣ የዕሪያ ደም እንደሚያቀርብልኝ ሰው ነው፤ የመታሰቢያን ዕጣን የሚያጥንልኝም፣ ጣዖትን እንደሚያመልክ ሰው ነው፤ የገዛ መንገዳቸውን መርጠዋል፤ ነፍሳቸውም በርኩሰታቸው ደስ ይላታል።


ዳሩ ግን አምላካችሁ እግዚአብሔር ለስሙ ማደሪያ እንዲሆነው፣ በነገዶቻችሁ መካከል የሚመርጠውን ስፍራ እሹ፤ ወደዚያም ስፍራ ሂዱ።


ወደዚያም የሚቃጠሉ መሥዋዕቶቻችሁንና ሌሎች መሥዋዕቶቻችሁን፣ ዐሥራታችሁንና የእጃችሁን ስጦታ፣ ስእለቶቻችሁንና የበጎ ፈቃድ ስጦታችሁን፣ የቀንድ ከብት መንጋችሁን፣ የበግና የፍየል መንጋዎቻችሁን በኵራት አምጡ።


ሳኦልም አኪያን፣ “የእግዚአብሔርን ታቦት ወደዚህ አምጣ” አለው፤ በዚያ ጊዜ ታቦቱ በእስራኤላውያን ዘንድ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች