Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሩት 2:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ለናዖሚም ሀብታምና ታዋቂ የሆነ ቦዔዝ የሚባል የባልዋ የአቤሜሌክ የቅርብ ዘመድ ነበራት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ኑኃሚን፣ ከአሊሜሌክ ጐሣ የሆነ ቦዔዝ የሚባል ባለጠጋ የባል ዘመድ ነበራት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ለናዖሚም በባልዋ የሚዛመዳት ሰው ከኤሊሜሌክ ወገን የሆነ ስሙ ቦዔዝ የተባለ ኃያል ሰው ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ለኑኃሚንም ባል የሚዛመደው ከአቤሜሌክ ወገን የሆነ ኃያል ሰው ስሙ ቦዔዝ የተባለ ሰው ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ለኑኃሚንም ባል የሚዘመደው ከአቤሜሌክ ወገን የሆነ ኃያል ሰው ስሙ ቦዔዝ የተባለ ሰው ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሩት 2:1
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ምናሔም ገንዘቡን የሰበሰበው የእስራኤል ከበርቴዎች እያንዳንዳቸው ኀምሳ ጥሬ ብር አዋጥተው እንዲሰጡ በማስገደድ ነበር። በዚህም ዐይነት ቲግላት ፐሌሴር በሰላም ወደ አገሩ ተመልሶ ሄደ።


በሀብትም በኩል ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመሎች፥ አምስት መቶ ጥማድ በሬዎችና አምስት መቶ አህዮች ነበሩት፤ እንዲሁም እጅግ ብዙ አገልጋዮች ነበሩት፤ በምሥራቅ አገር ካሉት ሰዎች ሁሉ እርሱን የሚያኽል ሀብታምና ታላቅ ሰው አልነበረም።


‘ሀብቴ በዝቷል፥ በብልጽግናዬም ብዙ ገንዘብ አግኝቼአለሁ’ ብዬ ተደስቼ አላውቅም።


ሰልሞን ቦዔዝን ረዓብ ከምትባል ሴት ወለደ፤ ቦዔዝ ኢዮቤድን ሩት ከምትባል ሴት ወለደ፤ ኢዮቤድ እሴይን ወለደ፤


ዳዊት የእሴይ ልጅ፥ እሴይ የኢዮቤድ ልጅ፥ ኢዮቤድ የቦዔዝ ልጅ፥ ቦዔዝ የሰልሞን ልጅ፥ ሰልሞን የነአሶን ልጅ፥


የሰውዬው ስም ኤቤሜሌክ፥ የሚስቱ ስም ናዖሚ፥ የሁለቱ ልጆች ስም ማሕሎንና ኬሌዎን ይባል ነበር፤ በትውልዱ ኤፍራታዊ ሆኖ በቤተልሔም ከተማ የሚኖር ነበር፤ እርሱም ከቤተሰቡ ጋር ወደ ሞአብ አገር ሄዶ ኖረ።


አንድ ቀን ሞአባዊትዋ ሩት ናዖሚን “በፊቱ ሞገስ ወደማገኝበት ሰው እርሻ ሄጄ ቃርሚያ ልቃርም” አለቻት። ናዖሚም “ልጄ ሆይ! ሂጂ!” አለቻት።


እኔ የቅርብ ዘመድ መሆኔ እውነት ነው፤ ነገር ግን ከእኔ ይልቅ ቅርብ የሆነ ሌላ ዘመድ አለ፤


ስትቃርሚ አብረውሽ የነበሩት ሴቶች የሚያገለግሉት ቦዔዝ የቅርብ ዘመዳችን ነው፤ እነሆ! እርሱ ዛሬ ማታ ገብስ ይወቃል፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች