Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 96:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 በዙሪያው ያለው ክብርና ግርማ ነው፤ ኀይልና ውበትም በመቅደሱ ውስጥ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ክብርና ግርማ በፊቱ ናቸው፤ ብርታትና ክብርም በመቅደሱ ውስጥ አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ክብርና ግርማ በፊቱ፥ ኃይልና ውበት በመቅደሱ ውስጥ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ሰማ​ያት የእ​ር​ሱን ጽድቅ አወሩ፥ አሕ​ዛ​ብም ሁሉ ክብ​ሩን አዩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 96:6
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዙሪያው ያለው ክብርና ግርማ ነው፤ መቅደሱንም ኀይልና ደስታ እንዲሞላበት አድርጎአል።


ነፍሴ ሆይ! እግዚአብሔርን አመስግኚ! እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! እንዴት ታላቅ ነህ! ግርማንና ክብርን ለብሰሃል።


ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፤ የሰማይ ጠፈርም፥ የእጁን ሥራ ያውጃል።


እግዚአብሔርን አንድ ነገር እለምነዋለሁ፤ የምለምነውም፦ በሕይወት ዘመኔ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ የእግዚአብሔርን አስደናቂነት እንድመለከትና በቤተ መቅደሱም መጸለይ እንድችል ነው።


የእግዚአብሔር ድምፅ አጋዘንን እንድትወልድ ያደርጋል የዛፎችን ቅጠል ያረግፋል፤ በመቅደሱም ያሉ ድምፁን ሲሰሙ “ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን!” ይላሉ።


እግዚአብሔር በውበትዋ ፍጹም ከሆነችው ከጽዮን ከተማ የደመቀ ብርሃንን ያበራል።


ሰው መልካም ምግብ በልቶ እንደሚጠግብ ነፍሴ በአንተ ትረካለች፤ ስለዚህ የምስጋና መዝሙር በደስታ እዘምርልሃለሁ።


ጌታችንና እግዚአብሔር ሆይ! ስምህ በዓለም ሁሉ የገነነ ነው። ክብርህንም ከሰማያት ሁሉ በላይ አድርገሃል።


እግዚአብሔር ንጉሥ ነው፤ ግርማንና ኀይልን ተጐናጽፎአል፤ ምድርን በአንድ ስፍራ አጸናት፤ ከቶም አትናወጥም።


እርሱ የእግዚአብሔር ክብር ነጸብራቅ ነው፤ እርሱ በባሕርዩ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም ትክክል ነው። በኀያል ቃሉ ዓለምን ሁሉ ደግፎ ይዞአል፤ ሰዎችንም ከኃጢአት ካነጻ በኋላ በሰማይ በኀያሉ እግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦአል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች