Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 78:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ሕዝቤ ሆይ! ትምህርቴን አድምጥ፤ ቃሌንም በጥንቃቄ ስማ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ሕዝቤ ሆይ፤ ትምህርቴን ስማ፤ ጆሮህንም ወደ አንደበቴ ቃል አዘንብል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 የአሳፍ ትምህርት። ሕዝቤ ሆይ፥ ሕጌን አድምጡ፥ ጆሮአችሁንም ወደ አፌ ቃል አዘንብሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 አቤቱ፥ አሕ​ዛብ ወደ ርስ​ትህ ገቡ፤ ቤተ መቅ​ደ​ስ​ህ​ንም አረ​ከሱ፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም እንደ ተክል ጠባቂ ጎጆ አደ​ረ​ጉ​አት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 78:1
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኀያሉ እግዚአብሔር አምላክ ይናገራል፤ ከፀሐይ መውጫ እስከ መጥለቂያዋ ድረስ፥ በምድር ያለውን ሰው ሁሉ ይጠራል።


ቀጥሎም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “ሕዝቤ ሆይ! ቃሌን ስማ፤ እስራኤል ሆይ! በአንተ ላይ እመሰክራለሁ፤ እኔ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ።


እኔ ያመፅኩት በአንተ ላይ ነው፤ የበደልኩትም አንተን ብቻ ነው፤ አንተ የምትጠላውን ነገር አደረግሁ፤ ስለዚህ በእኔ ላይ መፍረድህና እኔንም መቅጣትህ ትክክል ነው።


አምላክ ሆይ! እንደዚህ ለምን ተውከን? ሕዝብህንስ የምትቈጣው ለዘለዓለም ነውን?


ጠቢባን ሰዎች የተናገሩትን ሳስተምርህ አድምጥ፤ ከእነርሱ የምታገኘውን ትምህርት አጥና፤


“ሕዝቤ ሆይ! ስሙ! የምላችሁንም አድምጡ ሕግ ከእኔ ይገኛል፤ ፍርዴም ለሕዝቦች ሁሉ ብርሃን ይሆናል።


“ጆሮአችሁን አዘንብላችሁ ወደ እኔ ቅረቡ፤ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ቃሌን አድምጡ፤ ዳዊትን እንደ ወደድኩት እናንተን በታማኝነት ለመውደድ ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን እገባለሁ።


ሰሚ ጆሮ ያለው ይስማ!”


እናንተ ነገሥታት ስሙ! እናንተም አለቆች አድምጡ! እኔ ለእግዚአብሔር፥ እዘምራለሁ፤ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር አዜማለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች