Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 72:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ንጉሡ ሣሩ በታጨደ መስክ ላይ እንደሚዘንብ ዝናብ፥ በምድርም ላይ እንደሚወርድ ካፊያ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 እንደ ዝናብ በታጨደ መስክ ላይ ይወርዳል፤ እንደ ካፊያም ምድርን ያረሰርሳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እንደ ዝናብ በታጨደ መስክ ላይ፥ በምድርም ላይ እንደሚንጠባጠብ ጠብታ ይውረድ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ስለ​ዚ​ህም ትዕ​ቢት ያዛ​ቸው፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንና በደ​ላ​ቸ​ውን ተጐ​ና​ጸ​ፉ​አት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 72:6
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኑ፤ እግዚአብሔርን እንወቅ፤ ሳናወላውልም እንከተለው፤ እርሱም እንደ ንጋት ብርሃንና ምድርን እንደሚያረካ የበልግ ዝናም በእርግጥ ወደ እኛ ይመጣል።”


ትምህርቴ እንደ ዝናብ ይዝነብ፤ ንግግሬም እንደ ጤዛ ይንጠባጠብ፤ በሣር ላይ እንደ ለስላሳ ዝናብ፥ በቡቃያም ላይ እንደሚወርድ ካፊያ፥


ከዝናብ በኋላ ደመና እንደሌለው ንጋት፥ ምድርንም ሣር እንድታበቅል እንደሚያደርግ፥ እንደ ንጋት የፀሐይ ብርሃን ነው።”


ለታረሱ ማሳዎች በቂ ዝናብ ትሰጣለህ፤ ወጣ ገባውን ታስተካክላለህ፤ ዐፈሩንም በካፊያ ታለሰልሳለህ፤ ቡቃያዎችም በቅለው እንዲያድጉ ታደርጋለህ።


ከዚያን በኋላ አይገረዝም፤ አይኰተኰትም፤ ስለዚህም አራሙቻ እንዲበቅልበት፥ በኲርንቺትና በእሾኽ እንዲሸፈን አደርጋለሁ፤ ዝናብም እንዳያዘንብበት ደመናን አዛለሁ።”


የንጉሥ ቊጣ እንደ አንበሳ ጩኸት አስፈሪ ነው፤ ከንጉሥ ዘንድ የሚገኝ ሞገስ ግን ሣርን እንደሚያለመልም ጠል ነው።


የንጉሥ ፈገግታ ሕይወት ነው፤ ከእርሱም ተወዳጅነትን ማግኘት እንደ በልግ ዝናብ ልምላሜን ይሰጣል።


የናምሩድ ግዛት የነበረችውንም በሠራዊታቸው ኀይል አሦርን ድል ነሥተው ይይዛሉ፤ አሦራውያን አገራችንን ቢወሩና ድንበራችንን ቢረግጡ እርሱ ከእጃቸው ያድነናል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች