Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 69:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ለቤትህ ያለኝ ቅናት በውስጤ እንደ እሳት ይነዳል፤ በአንተ ላይ የተሰነዘረው ስድብ በእኔ ላይ ዐረፈ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 የቤትህ ቅናት በላችኝ፤ የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ዐርፏል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ለወንድሞቼ እንደ ሌላ፥ ለእናቴ ልጆችም እንደ እንግዳ ሆንሁባቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 69:9
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኤልያስም “ሁሉን የምትችል አምላኬ ሆይ! እኔ ለአምላክነትህ በመቅናት ዘወትር አንተን ብቻ አገለግላለሁ፤ የእስራኤል ሕዝብ ግን ከአንተ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል፤ መሠዊያዎችህንም ሰባብረዋል፤ ነቢያትህንም ሁሉ ገድለዋል፤ እነሆ እኔ ብቻዬን ቀርቻለሁ፤ እነርሱ ግን እኔንም እንኳ ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ!” ሲል መለሰ።


ከእነዚህ ካዘጋጀኋቸው ነገሮች ሁሉ በላይ እኔ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ካለኝ ታላቅ ፍቅር የተነሣ ከራሴ ንብረት ብዙ ብርና ወርቅ ሰጥቼአለሁ፤


“እግዚአብሔር ወንድሞቼ ከእኔ እንዲርቁ አደረገ፤ የሚያውቁኝም ሰዎች ሁሉ ባይተዋር አደረጉኝ።


ጠላቶቼ ትእዛዞችህን አለመቀበላቸው በጣም ያበሳጨኛል።


ሊገድሉኝ የሚፈልጉ ወጥመድ ይዘረጉብኛል፤ ሊጐዱኝ የሚያቅዱ ሊያጠፉኝ ይዝታሉ፤ በእኔም ላይ ቀኑን ሙሉ ያሤራሉ።


የመንገድ ተላላፊዎች ሁሉ ንብረቱን ይዘርፋሉ፤ የጐረቤቶቹ መሳለቂያ ሆኖአል።


ክርስቶስ ራሱን አላስደሰተም፤ ይልቁንም “ሰዎች አንተን የሰደቡበት ስድብ በእኔ ላይ ወረደ” የሚለው የቅዱሳት መጻሕፍት አባባል ደረሰበት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች