Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 69:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 በበደላቸው ላይ በደልን ጨምርባቸው፤ ይቅርታም አታድርግላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 በበደላቸው በደል ጨምርባቸው፤ ወደ ጽድቅህም አይግቡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 አንተ የቀሠፍኸውን እነርሱ አሳድደዋልና፥ ባቈሰልከውም ላይ ጥዝጣዜ ጨመሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 69:27
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለሚያደርጉት ክፉ ነገር ምሕረት አታድርግላቸው፤ የፈረሰውን በመሥራታችን በስድብ አዋርደውናልና በደላቸውን አትርሳ።”


እግዚአብሔር እንዳሳደደኝ እናንተ ደግሞ ለምን ታሳድዱኛላችሁ? እስካሁንስ ያሠቃያችሁኝ አይበቃችሁምን?


እግዚአብሔር የቀድሞ አባቶቹን ኃጢአት ያስብበት፤ የእናቱንም ኃጢአት ይቅር አይበልላት።


እንዲህ ዐይነቱ ሰው ከአዳኝ አምላኩ ከእግዚአብሔር በረከትንና ፍትሕን ይቀበላል።


ስለዚህ በልበ ደንዳናነታቸው አካሄድ እንዲሄዱ፥ የፈለጉትንም ነገር እንዲያደርጉ ተውኳቸው።


ንጉሡ ጓጒንቸሮቹ መሞታቸውን ባየ ጊዜ እግዚአብሔር እንዳለው ልቡን አደንድኖ አልሰማቸውም።


ይሁን እንጂ ንጉሡ አሁንም ልቡን በማደንደን የእስራኤልንም ሕዝብ አለቀቀም።


ነገር ግን አሁንም እግዚአብሔር የንጉሡን ልብ በማደንደን እግዚአብሔር አስቀድሞ ለሙሴ እንደ ተናገረ ንጉሡ ሙሴንና አሮንን አላደመጣቸውም።


ክፉ ሰዎች ቸርነት ብታደርግላቸው እንኳ መልካም መሥራትን አይማሩም፤ በዚህ ጽድቅ በሰፈነበት ምድር እያሉ እንኳ ክፋት ከማድረግ አይቈጠቡም፤ ታላቅነትህንም አይገነዘቡም።


ከዚያን በኋላ አይገረዝም፤ አይኰተኰትም፤ ስለዚህም አራሙቻ እንዲበቅልበት፥ በኲርንቺትና በእሾኽ እንዲሸፈን አደርጋለሁ፤ ዝናብም እንዳያዘንብበት ደመናን አዛለሁ።”


“በእውነት እርሱ ደዌአችንን ተቀበለ፤ ሕማማችንንም ተሸከመ፤ እኛ ግን በእግዚአብሔር ተመትቶ እንደ ወደቀና እንደ ቈሰለ አድርገን ቈጠርነው።


በጠላቶቻችሁ ምድር ከሞት ተርፋችሁ የምትቀሩት ጥቂቶቻችሁ፥ በራሳችሁና በቀድሞ አባቶቻችሁ ኃጢአት ምክንያት መንምናችሁ ትቀራላችሁ።


አንዲት የበለስ ዛፍ በመንገድ ዳር አየና ወደ እርስዋ ሄደ፤ ነገር ግን ከቅጠል በቀር ምንም አላገኘባትም። ስለዚህ “ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ ፍሬ አይገኝብሽ!” አላት። ዛፊቱም ወዲያውኑ ደረቀች።


ሰዎች እግዚአብሔርን ለማወቅ ስላልፈለጉ አስነዋሪ ነገር እንዲያደርጉ እግዚአብሔር ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው።


ስለዚህ እግዚአብሔር የሚፈልገውን ይምረዋል፤ የሚፈልገውንም እልኸኛ ያደርገዋል።


ነገር ግን ጽድቅ የሚያስገኘውን ሕግ ይከተሉ የነበሩት እስራኤላውያን ሕግን ለመፈጸም ባለመቻላቸው ወደ ጽድቅ አልደረሱም።


የናስ አንጥረኛው እስክንድር ከፍተኛ ጒዳት አደረሰብኝ፤ ጌታ እንደ ሥራው ይከፍለዋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች