24 ኀይለኛ ቊጣህን በላያቸው አፍስስ፤ የቊጣህ መቅሠፍትም ይድረስባቸው።
24 መዓትህን በላያቸው አፍስስ፤ የቍጣህም መቅሠፍት ድንገት ይድረስባቸው።
24 ዐይኖቻቸው እንዳያዩ ይጨልሙ፥ ወገባቸውም ዘወትር ይንቀጥቀጥ።
ቊጣህን አንተን በአምላክነትህ ወደማያውቁና ወደ አንተ ወደማይጸልዩ ሕዝቦችና መንግሥታት ላይ መልስ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የይሁዳ መሪዎች የእስራኤልን ድንበር እንደሚያፈርሱ ሰዎች ሆነዋል፤ ስለዚህ እኔ ቊጣዬን እንደ ጐርፍ ውሃ አወርድባቸዋለሁ።
ከዚህ በኋላ ሰባቱን መላእክት “ሂዱ! የእግዚአብሔርን ቊጣ የያዙትን ሰባቱን ጽዋዎች በምድር ላይ አፍስሱ!” የሚል ከፍ ያለ ድምፅ ከቤተ መቅደስ ሲወጣ ሰማሁ።
ስለዚህ ጥፋት የተጻፈው ትንቢት እንዲፈጸም ይህ የበቀልና የቅጣት ጊዜ ነው።
ነገር ግን አገልጋዮቼ በሆኑት በነቢያት አማካይነት ለቀድሞ አባቶቻችሁ ያስተላለፍኩትን ሕግና ትእዛዝ ባለመጠበቃቸው ተቀጥተው የለምን? ስለዚህ በበደላቸው ተጸጸተው ‘የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ባቀደው መሠረት እንደ ሥራችንና እንደ አካሄዳችን በእኛ ላይ ቅጣትን ማምጣቱ ትክክለኛ ነው’ አሉ።”
የምትወልድ ሴት በምጥ እንደምትሠቃይ እነርሱም በፍርሃት ይሠቃያሉ፤ እርስ በርሳቸው በፍርሃት ይተያያሉ።
ይህም በሚሆንበት ጊዜ እኔ በእነርሱ ላይ ተቈጥቼ እለያቸዋለሁ፤ ፊቴን ከእነርሱ እሰውራለሁ፤ እነርሱም ይደመሰሳሉ፤ በእነርሱም ላይ ብዙ አሠቃቂ መቅሠፍት ይመጣባቸዋል፤ በዚያን ጊዜ፥ ‘ይህ ችግር የመጣብን አምላካችን በመካከላችን ስለሌለ አይደለምን?’ ይላሉ።
የኤዶም መሪዎች ተስፋ ቈረጡ፤ የሞአብም ኀያላን ተንቀጠቀጡ፤ የከነዓንም ሕዝብ ወኔ ከዳቸው።