Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 48:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 አምላክ ሆይ! በመቅደስህ ውስጥ ስለ ዘለዓለማዊው ፍቅርህ እናስባለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 አምላክ ሆይ፤ በቤተ መቅደስህ ውስጥ ሆነን፣ ምሕረትህን እናስባለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እንደ ሰማን እንዲሁ አየን በሠራዊት ጌታ ከተማ፥ በአምላካችን ከተማ፥ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ያጸናታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 በዓ​ለም የደ​ከመ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይድ​ናል፥ ጥፋ​ትን አያ​ይ​ምና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 48:9
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የማያቋርጠው ፍቅርህ በዐይኖቼ ፊት ነው፤ ዘወትር የሚመራኝም የአንተ ታማኝነት ነው።


ደግነትህን በልቤ ውስጥ አልደብቅም፤ ስለ ታማኝነትህና ስለ አዳኝነትህ ተናግሬአለሁ፤ ከትልቁ ጉባኤ ዘለዓለማዊ ፍቅርህንና እውነተኛነትህን አልሰውርም።


እጄን ይዘህ ሳበኝ፤ አብረን እንሩጥ። ንጉሡ ወደ እልፍኙ አስገባኝ፤ በዚያም አብረን ደስ ይለናል፤ ፍቅርህ ከወይን ጠጅ ይልቅ ያስደስታል፤ ስለዚህ ቈነጃጅት ሁሉ እጅግ ያፈቅሩሃል።


ደስታዬ በእርሱ ስለ ሆነ እርሱም በማቀርብለት የተመስጦ ጸሎት ደስ ይበለው።


አምላክ ሆይ፥ ሕግህን እየጠበቅን በአንተ ተስፋ እናደርጋለን። የልባችንም ምኞት የአንተ ገናናነት በሕዝቦች ዘንድ እንዲታወቅ ማድረግ ነው።


ንጉሥ ሰሎሞንንም እንዲህ አለችው፦ “ስለ ሥራህ ውጤትና ስለ ጥበብህ ታላቅነት በአገሬ ሳለሁ የሰማሁት ሁሉ እውነት ነው!


ነገር ግን እዚህ ድረስ መጥቼ በዐይኔ እስካየው ድረስ የተነገረኝን ሁሉ አላመንኩም ነበር፤ በጆሮዬ የሰማሁት በዐይኔ ያየሁትን እኩሌታ እንኳ አይሆንም፤ በእርግጥም ጥበብህና ሀብትህ በአገሬ ሳለሁ ከተነገረኝ በጣም ይበልጣል።


ልዑል እግዚአብሔር ራሱ ስለሚመሠርታት ስለ ጽዮን፦ “ይህም ሕዝብ፥ ያም ሕዝብ በእርስዋ ውስጥ ተወልደዋል” ይባላል።


በድንና ዐመድ የሚጣልበት መላው ሸለቆ በምሥራቅ በኩል እስከ ፈረስ በር ድረስ እንኳ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል፤ ከተማይቱም እንደገና ከቶ አትፈርስም፤ አትደመሰስምም።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች