Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 41:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ድኾችን የሚረዱ የተባረኩ ናቸው፤ እነርሱም በተቸገሩ ጊዜ እግዚአብሔር ይረዳቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ብፁዕ ነው፤ ለድኾች የሚያስብ፤ እግዚአብሔር በክፉ ቀን ይታደገዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ዋሊያ ወደ ውኃ ምን​ጮች እን​ደ​ሚ​ና​ፍቅ፥ እን​ዲሁ ነፍሴ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትና​ፍ​ቃ​ለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 41:1
27 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለድኾች የሚሰጥ ለእግዚአብሔር እንዳበደረ ይቈጠራል፤ እግዚአብሔርም የመልካም ሥራውን ዋጋ ይከፍለዋል።


ሰዎችን የሚንቅ ኃጢአተኛ ነው፤ ለድኾች የሚራራ ግን የተባረከ ነው፤


‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ የተባረከ ነው’ የሚለውን የጌታ ኢየሱስን ቃል በማስታወስ፥ በእጃችን እየሠራን ደካሞችን መርዳት እንደሚገባን በብዙ መንገድ አሳይቻችኋለሁ።”


የእግዚአብሔር ፍርድ ምሕረት ለማያደርግ ሰው ምሕረት አያደርግም፤ ሆኖም ምሕረት ፍርድን ያሸንፋል።


እግዚአብሔር ቅን ፈራጅ ነው፤ ስለዚህ ሥራችሁንና በፊትም ሆነ አሁን ቅዱሳንን በመርዳት ስለ ስሙ ያሳያችሁትን ፍቅር አይረሳም።


ክፉ ቀን ሲመጣ ችግር አይደርስባቸውም፤ በራብ ዘመንም በቂ ምግብ በማግኘት ይጠግባሉ።


ለችግረኞች በልግሥና ይሰጣል፤ ቸርነቱም የማያቋርጥ ነው፤ ኀይልንና ክብርን ይጐናጸፋል።


ድኾች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ስለ ሆኑ በፈለጋችሁ ጊዜ ልትረዱአቸው ትችላላችሁ፤ እኔን ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አታገኙኝም፤


ደግ ሰው ሁልጊዜ በልግሥና ይሰጣል፤ እንዲሁም ያበድራል፤ ልጆቹም የተባረኩ ይሆናሉ።


ትዕግሥተኛ ሁን ያልኩህን ቃሌን ስለ ጠበቅህ እኔም በምድር ላይ የሚኖሩትን ሊፈትናቸው በዓለም ሁሉ ላይ ከሚመጣው ከመከራ ሰዓት እጠብቅሃለሁ።


ብቻ በመካከላቸው ያሉትን ድኾች እንድናስታውስ ዐደራ አሉን፤ ይህም እኔ በትጋት ያደረግኹት ነገር ነው።


ወንድሞች ሆይ! “ሰነፎችን ገሥጹ፤ ፈሪዎችን አደፋፍሩ፤ ደካሞችን እርዱ፤ ሰውን ሁሉ ታገሡ” ብለን እንመክራችኋለን።


የንጉሥ ቊጣ የሞት መልእክተኛ ነው። ብልኅ ሰው ግን ቊጣውን ያበርዳል።


ጻድቅ ብዙ መከራ ይደርስበታል፤ እግዚአብሔር ግን ከዚህ ሁሉ ያድነዋል።


በወጣትነትህ ዘመን ፈጣሪህን አስብ፤ ይህን ባታደርግ ግን ክፉ ቀን ይመጣብሃል፤ “ደስ አያሰኙኝም” የምትላቸው ዓመቶች ይደርሳሉ።


ዐማትዋ “ዛሬ ከየት ቃረምሽ? ወደየትስ ሠራሽ? ይህን መልካም አቀባበል ያደረገልሽን ሰው እግዚአብሔር ይባርከው!” አለቻት። ሩትም “እኔ ስቃርም የዋልኩበት እርሻ ባለቤት ቦዔዝ የሚባል ሰው ነው” ብላ ለናዖሚ ነገረቻት።


ነገር ግን በዚያን ቀን እኔ እግዚአብሔር አንተን አድንሃለሁ፤ ለምትፈራቸው ጠላቶችህ ተላልፈህ አትሰጥም፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች