Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 40:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 በትልቁ ጉባኤ ፊት ትክክለኛውን ነገር ተናገርኩ፤ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ እንደምታውቀው ቃሌን ከመናገር አልቈጥበውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 በታላቅ ጉባኤ ውስጥ ጽድቅን አበሠርሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ እንደምታውቀው፣ ከንፈሮቼን አልገጠምሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድሁ፥ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ደግሞ የሰ​ላሜ ሰው የታ​መ​ን​ሁ​በት፥ እን​ጀ​ራ​ዬን የበላ በእኔ ላይ ተረ​ከ​ዙን አነሣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 40:9
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለ ሠራኸው መልካም ሥራ ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበበት ስፍራ አመሰግንሃለሁ፤ በሚፈሩህ ሰዎች ፊት ሆኜ፥ የተሳልኩትን ስለት እፈጽማለሁ።


አንተ የሰጠኸውን ሕግ ሁሉ መላልሼ አነባለሁ።


የስምህን ታላቅነት ለወገኖቼ እናገራለሁ፤ እነርሱ በተሰበሰቡበት ስፍራ አመሰግንሃለሁ፤


ስለዚህም በቅዱሳት መጻሕፍት “ስምህን ለወንድሞቼ አበሥራለሁ፤ በማኅበርም መካከል በዜማ አመሰግንሃለሁ” ይላል፤


በዚያን ጊዜ በሕዝብ ጉባኤ መካከል ሆኜ አመሰግንሃለሁ፤ ብዙ ሕዝብም በተሰበሰበበት ቦታ አከብርሃለሁ።


“ከሁሉ የሚበልጥ ኀያል እግዚአብሔር ነው! እርሱ የሁሉ ጌታ ነው! እርሱ ከሁሉ የሚበልጥ ኀያል አምላክ ነው! እኛ ስለምን ይህን እንደ ሠራን እርሱ ያውቃል፤ እናንተም ስለምን እንደ ሠራነው እንድታውቁት እንፈልጋለን፤ በእውነት ካመፅንና በእግዚአብሔር ላይ ያለንን እምነት አጓድለን ከተገኘን፥ በሕይወት እንድንኖር አትፍቀዱልን፤


ሦስተኛ ጊዜም “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! ትወደኛለህን?” አለው። ሦስተኛ ጊዜ “ትወደኛለህን?” ስላለው ጴጥሮስ አዘነና “ጌታ ሆይ! አንተ ሁሉን ታውቃለህ፥ እኔ እንደምወድህም ታውቃለህ” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “በጎቼን አሰማራ፤


አንተ ስቀመጥም ሆነ ስነሣ ታውቃለህ፤ ሐሳቤን ሁሉ ከሩቅ ሆነህ ታስተውላለህ።


የአምላኩም ሕግ በልቡ ነው፤ እግሩም አይደናቀፍም።


እነሆ ከዚህ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፤ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች