Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 40:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ከረግረግ ቦታና ጭቃማ ከሆነው ከሚያዳልጥ ጒድጓድ አወጣኝ፤ እግሮቼን በአለት ድንጋይ ላይ አድርጎ የምቆምበትን ጠንካራ ቦታ ሰጠኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ከሚውጥ ጕድጓድ፣ ከሚያዘቅጥ ማጥ አወጣኝ፤ እግሮቼን በዐለት ላይ አቆመ፤ አካሄዴንም አጸና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በትዕግሥት ጌታን ደጅ ጠናሁት፥ እርሱም ዘንበል አለልኝ ጩኸቴንም ሰማኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጠ​ብ​ቀ​ዋል፥ ሕያ​ውም ያደ​ር​ገ​ዋል፥ በም​ድር ላይም ያስ​መ​ሰ​ግ​ነ​ዋል፥ በጠ​ላ​ቶቹ እጅ አሳ​ልፎ አይ​ሰ​ጠ​ውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 40:2
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግዚአብሔር በሰው አካሄድ ከተደሰተ የእርምጃውን ትክክለኛነት ያረጋግጥለታል።


በተስፋ ቃልህ መሠረት አካሄዴን አስተካክል፤ ስሕተትም እንዲሠለጥንብኝ አታድርግ።


በችግር ቀን በጥላው ሥር ይደብቀኛል፤ በመቅደሱ ውስጥ ይሰውረኛል፤ በአለትም ላይ ከፍ አድርጎ ይጠብቀኛል።


ተስፋ ቈርጬ ሳለ ከሩቅ አገር ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ከእኔ በላይ ወደ አለው ከፍተኛ አምባ ምራኝ።


በብዙ ችግርና መከራ እንድሠቃይ አድርገኸኛል፤ ሆኖም እንደገና ከመሬቱ ጥልቅ ጒድጓድ አውጥተህ አዲስ ሕይወትን ትሰጠኛለህ።


ለእኔ የምታሳየው ዘለዓለማዊው ፍቅርህ እንዴት ታላቅ ነው! ወደ ሲኦል ጥልቀት ከመውረድ አዳንከኝ።


መቆሚያ ስፍራ ስለ አጣሁ በጥልቅ ረግረግ ውስጥ ለመስረግ ተቃርቤአለሁ፤ በጥልቅ ውሃ ውስጥ እገኛለሁ፤ ውሃ ሙላት ሊያሰጥመኝ ተቃርቦአል።


“በመሥዋዕት ደም ከአንቺ ጋር ቃል ኪዳን ስለ ገባሁ፥ ውሃ ከማይገኝበት ጒድጓድ እስረኞችሽን ነጻ አወጣለሁ።


መረማመጃዬን አሰፋህ፤ እግሮቼም አልተንሸራተቱም።


እግዚአብሔር ግን የሞትን ኀይል አስወግዶ ከሞት አስነሣው፤ ስለዚህም ሞት ይዞ ሊያስቀረው አልቻለም።


ጠላቴ በማሳደድ ተከታተለኝ፤ በጨለማ ውስጥም አስሮ አጐሳቈለኝ፤ ከብዙ ዘመናት በፊት እንደ ሞቱ ሰዎች ሆኜአለሁ።


ዘወትር በመንገድህ ተራመድኩ፤ ከመንገድህም ወጥቼ አልባዘንኩም።


የሞት አደጋ ዙሪያዬን ከበበኝ፤ የመቃብር አስፈሪ ሁኔታ አሠቀቀኝ፤ በችግርና በሐዘን ተሸነፍኩ።


ክፉዎችን ወደ እቶን እሳትም ይጥሉአቸዋል፤ በዚያ ለቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።”


እግዚአብሔር ነገሥታትን በአንድነት ሰብስቦ በምድር ውስጥ ባለ እስር ቤት ውስጥ እንዳሉ እስረኞች እንዲኖሩ ያደርጋል፤ ከብዙ ቀኖችም በኋላ ይቀጣቸዋል።


እግዚአብሔር ስለ ተቈጣ ምድር ተናወጠች፤ ተንቀጠቀጠችም፤ የተራሮች መሠረቶች ተናጉ፤ ተነቃነቁም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች