Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 40:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እግዚአብሔር ሆይ! ምሕረትህን ከእኔ አታርቅ፤ ፍቅርህና ዘለዓለማዊ ታማኝነትህ ለዘለዓለም ይጠብቁኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህን አትንፈገኝ፤ ቸርነትህና እውነትህ ዘወትር ይጠብቁኝ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 አዳኝ ጽድቅህን በልቤ ውስጥ አልሰወርኩም፥ ታማኝነትህንና ማዳንህንም ተናገርሁ፥ ጽኑ ፍቅርህንና እውነትህን ከታላቅ ጉባኤ አልደበቅሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ስለ​ዚህ እንደ ወደ​ድ​ኸኝ ዐወ​ቅሁ። ጠላ​ቶቼ በእኔ ደስ አላ​ላ​ቸ​ውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 40:11
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በሕይወት ዘመኔ ሁሉ ደግነትና ፍቅር ሁልጊዜ ከእኔ ጋር ይሆናሉ፤ በምኖርበት ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖራለሁ።


ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እነርሱ እየመሩ ወደ ተቀደሰው ተራራህ፥ ወደ ማደሪያ መቅደስህም ያምጡኝ።


እግዚአብሔር ከሰማይ ልኮ ያድነኛል፤ የሚያስጨንቁኝንም ያዋርዳቸዋል፤ እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ፍቅሩንና ታማኝነቱን ይገልጣል።


አምላክ ሆይ! በፊትህ ለዘለዓለም እንዲነግሥ አድርገው፤ በዘለዓለማዊው ፍቅርህና በታማኝነትህ ጠብቀው።


እግዚአብሔር ሆይ! እኔ ግን ወደ አንተ እጸልያለሁ፤ አንተ በመረጥከው ጊዜ ጸሎቴን መልሰህ፥ በዘለዓለማዊው ፍቅርህ ማዳንህን አረጋግጥልኝ።


እግዚአብሔር ሆይ! ቸርነት በተሞላበት ፍቅርህ ጸሎቴን ስማ፤ በታላቁ ምሕረትህ ወደ እኔ ተመለስ።


ፍቅርና እውነት ይተቃቀፋሉ፤ ጽድቅና ሰላም ይስማማሉ።


ፍቅርህ ለዘለዓለም እንደሚጸናና ታማኝነትህን እንደ ሰማይ እንደሚመሠረት እናገራለሁ።


ቸርነትና ታማኝነት ንጉሥን ይጠብቁታል፤ መንግሥቱም በእውነተኛነት ላይ ጸንቶ ይኖራል።


ኢየሱስ ሰው ሆኖ በዚህ ምድር በኖረበት ጊዜ ከሞት ሊያድነው ወደሚችል አምላክ በታላቅ ጩኸትና በብዙ እንባ ጸሎትንና ልመናን አቀረበ፤ በትሕትና ራሱን ታዛዥ በማድረጉ እግዚአብሔር ጸሎቱን ሰማው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች