Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 32:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እንዲገቱ ለማድረግ በልባብና በልጓም እንደሚመሩት እንደ ፈረስና እንደ በቅሎ የማይገባችሁ አትሁኑ። እንደዚያ ካላደረጋችሁ ፈረስና በቅሎ ወደ እናንተ አይቀርቡም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 በልባብና በልጓም ካልተገሩ በቀር፣ ወደ አንተ እንደማይቀርቡት፣ ማስተዋል እንደሌላቸው፣ እንደ ፈረስና እንደ በቅሎ አትሁኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ወደ አንተ እንዳይቀርቡ በልባብና በልጓም ጉንጫቸውን እንደሚለጉሙአቸው፥ ልብ እንደሌላቸው እንደ ፈረስና እንደ በቅሎ አትሁኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እርሱ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና፥ ሆኑ፤ እርሱ አዘዘ፤ ተፈ​ጠ​ሩም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 32:9
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ፈረስን መግረፍ በቅሎንም መለጐም እንደሚያስፈልግ ሁሉ ሰነፍንም መቅጣት ያስፈልጋል።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤ እኔን የማያውቁ ሞኞች ሆነዋል፤ ማስተዋል ስለ ጐደላቸው እንደ ሕፃናት የሚታለሉ ናቸው፤ ክፉ ነገር ለመሥራት የተራቀቁ ብልኆች ናቸው፤ መልካም ነገር ማድረግ ግን ከቶ አይሆንላቸውም።”


ከእንስሶች አብልጦ ያስተማረን ከወፎችም ይልቅ ጥበበኞች ያደረገን እርሱ ነው።


ፈረስ እንዲታዘዝልን በአፉ ውስጥ ልጓም እናገባለን፤ ፈረሱንም ወደምንፈልገው ቦታ እንመራዋለን።


“የእስራኤል ሕዝብ በሐዘን እንዲህ ሲሉ ሰማኋቸው፤ ‘እግዚአብሔር ሆይ! እኛ እንዳልተገራ ወይፈን ነበርን፤ አንተ ግን መታዘዝን አስተማርከን፤ አንተ አምላካችን ስለ ሆንክ አሁንም ወደ አንተ ወደ አምላካችን መልሰን፤ እኛም እንመለሳለን።


እግዚአብሔር ኀይሌን አድክሞ ስላዋረደኝ፥ እነርሱ ልጓሙ እንደ ወለቀለት ፈረስ እንዳሻቸው ፈነጩብኝ።


ድርብርብ የሆነ ቆዳውን ለመግፈፍና መንጋጋውንስ ለመፈልቀቅ ማን ይችላል?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች