Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 23:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 በለመለመ መስክ እንዳርፍ ያደርገኛል፤ ሰላማዊ ወደ ሆነ የውሃ ጅረትም ይመራኛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 በለመለመ መስክ ያሳርፈኛል፤ በዕረፍት ውሃ ዘንድ ይመራኛል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፥ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እርሱ በባ​ሕ​ሮች መሥ​ር​ቶ​አ​ታ​ልና፥ በፈ​ሳ​ሾ​ችም አጽ​ን​ቶ​አ​ታ​ልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 23:2
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“እግዚአብሔርን የሚክድና ሕዝቡን የሚያጠምድ ንጉሥ ሲነግሥ፥ እግዚአብሔር ዝም ቢል፥ ወይም ፊቱን ቢሰውር ማን ሊወቅሰው ይችላል?


ጅረቶችዋ የልዑል እግዚአብሔርን ቅዱስ ማደሪያ፥ የአምላክን ከተማ የሚያስደስቱ አንዲት ወንዝ አለች።


ከዚህ በኋላ ወደ ኤሊም መጡ፤ በዚያም ስፍራ ዐሥራ ሁለት የውሃ ምንጮችና ሰባ የተምር ዛፎች ነበሩ፤ ሕዝቡም በዚያ ከውሃው አጠገብ ሰፈሩ።


ዘር በምትዘሩበት ጊዜ ቡቃያችሁን ለማሳደግና ብዙ መከር እንድታገኙ ለማድረግ እግዚአብሔር ዝናብን ይልክላችኋል፤ ከብቶቻችሁም ብዙ የመሰማሪያ ቦታ ያገኛሉ።


“በጸጥታ የሚሄደውን የሰሊሆምን ምንጭ ውሃ ትተው በንጉሥ ረጺንና በንጉሥ ፋቁሔ ተደስተዋል፤


ከዚህም በኋላ እንዲህ አለኝ፤ “ተፈጸመ! አልፋና ዖሜጋ፥ የመጀመሪያውና የመጨረሻው እኔ ነኝ፤ ለተጠማ ከሕይወት ውሃ ምንጭ ያለ ምንም ዋጋ በነጻ እሰጠዋለሁ፤


ከዚህ በኋላ መልአኩ ከእግዚአብሔርና ከበጉ ዙፋን የሚወጣውን እንደ ብሩህ መስተዋት ጥርት ያለውን የሕይወት ውሃ ወንዝ አሳየኝ፤


መንፈስ ቅዱስና ሙሽራይቱ “ና!” ይላሉ፤ የሚሰማም “ና!” ይበል፤ የተጠማም ይምጣ፤ የፈለገም የሕይወትን ውሃ ያለ ምንም ዋጋ በነጻ ይጠጣ።


በዙፋኑ መካከል ያለው በግ እረኛቸው ይሆናል፤ ወደ ሕይወት ውሃ ምንጭም ይመራቸዋል፤ እግዚአብሔር እንባን ሁሉ ከዐይናቸው ይጠርግላቸዋል።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች