Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 22:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 አምላኬ ሆይ! በቀን ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ አንተ ግን አትሰማኝም፤ በሌሊት እጣራለሁ፤ ዕረፍትም የለኝም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 አምላኬ ሆይ፤ በቀን ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ አንተ ግን አልመለስህልኝም፤ በሌሊት እንኳ አላረፍሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 አምላኬ፥ አምላኬ፥ ለምን ተውኸኝ? እኔን ከማዳንና ከጩኸቴ ለምን ራቅህ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 በለ​መ​ለመ መስክ ያሳ​ድ​ረ​ኛል፤ በዕ​ረ​ፍት ውኃ ዘንድ አሳ​ደ​ገኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 22:2
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግዚአብሔር ታዲያ፥ ሌት ተቀን እየጮኹ ለሚለምኑት ሕዝቦቹ አይፈርድላቸውምን? ችላ በማለትስ ርዳታውን ያዘገይባቸዋልን?


ቀንና ሌሊት ስለ ማልቅስ እንባዬ እንደ ምግብ ሆኖኛል፤ ጠላቶቼ “አምላክህ የት አለ?” እያሉ ዘወትር ይጠይቁኛል።


አዳኜ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! ትረዳኝ ዘንድ በቀን ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ሌሊቱንም በአንተ ፊት አለቅሳለሁ።


ዘወትር ሌሊትና ቀን አንተን በጸሎቴ ሳስታውስ አባቶቼ እንደ አደረጉት እኔም በንጹሕ ኅሊና የማገለግለውን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።


ሌሊትና ቀን በብርቱ የምንጸልየው በዐይነ ሥጋ እንድናያችሁና በእምነታችሁ የጐደለውን ለመሙላት እንድንችል ነው።


አንድ ቀን ኢየሱስ ለመጸለይ ወደ ተራራ ወጣ፤ እዚያ ሌሊቱን ሙሉ ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ ዐደረ።


እንደገናም ትቶአቸው ሄደና ያንኑ የፊተኛውን ቃል በመናገር ሦስተኛ ጊዜ ጸለየ።


ጸሎት አልፎ ሊገባ በማይችልበት ራስህን ጥቅጥቅ ባለ ደመና ሸፈንክ። መኖሪያህን በደመና ሸፈንክ።


ለእርዳታ ጩኸቴን ባሰማም እንኳ አላዳምጥ አለኝ።


የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! የሕዝብህን ጸሎት ባለመቀበል ቊጣህን የምትገልጠው እስከ መቼ ነው?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች