Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 22:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 መከራ ሊደርስብኝ ስለ ተቃረበና የሚረዳኝም ስለሌለ እባክህ ከእኔ አትራቅ!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 መከራ እየተቃረበ ነውና፣ የሚረዳኝም የለምና፣ ከእኔ አትራቅ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ከማኅፀን ጀምሮ በአንተ ላይ ተጣልሁ፥ ከእናቴ ሆድ ጀምረህ አንተ አምላኬ ነህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 22:11
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግዚአብሔር የእስራኤላውያንን አሠቃቂ መከራ ተመለከተ፤ በእስራኤል ውስጥ ባሪያዎችም ሆኑ ነጻ ሰዎች፥ ረዳት አልነበራቸውም።


እግዚአብሔር ሆይ! ስለምን እንደዚህ ርቀህ ትቆማለህ? በችግር ጊዜስ ስለምን ትሰወራለህ?


እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ይህን ተመልክተሃል፤ ስለዚህ ጌታ ሆይ! ዝም አትበል! ከእኔም አትራቅ!


እግዚአብሔር ሆይ! አትተወኝ፤ አምላኬ ሆይ! ከእኔ አትራቅ።


ወደ እኔ ቀርበህ ተቤዠኝ፤ ከጠላቶቼም አድነኝ።


አምላክ ሆይ! ከእኔ አትራቅ፤ አምላክ ሆይ! ፈጥነህ እርዳኝ።


በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በአንተ ላይ እታመናለሁ፤ ከእናቴ ማሕፀን እንድወለድ ያደረግኸኝ አንተ ነህ፤ እኔም ዘወትር አመሰግንሃለሁ።


ወደ እርሱ የሚጮኹትን ድኾች፥ ችግረኞችንና የተጨቈኑትን ሰዎች ነጻ ያወጣል።


ዙሪያዬን በተመለከትኩ ጊዜ የሚረዳ ማንም አልነበረም። ደጋፊ ባለመኖሩ ተደነቅሁ፤ ስለዚህ በኀይለኛ ቊጣዬ አማካይነት እኔው ራሴ ድልን አመጣሁ።


ነገር ግን ይህ ሁሉ የሆነው በነቢያት የተጻፈው እንዲፈጸም ነው።” በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ትተውት ሸሹ።


ጴጥሮስም “ይህን የምትዪውን ሰው አላውቀውም!” ሲል በመማል እንደገና ካደ።


በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ፦ “እኔ ይህን ሰው አላውቀውም!” እያለ ራሱን መራገምና መማል ጀመረ። ወዲያውኑ ዶሮ ጮኸ።


ይሁን እንጂ እያንዳንዳችሁ በየበኩላችሁ የምትበታተኑበትና እኔን ብቻዬን የምትተዉበት ሰዓት ይመጣል፤ ሰዓቱም አሁን ደርሶአል፤ ነገር ግን አብ ከእኔ ጋር ስለ ሆነ ብቻዬን አይደለሁም።


ኀይል ማጣታቸውን ሲያይ፥ እግዚአብሔር ለአገልጋዮቹ ይራራል፤ ነጻም፥ ባሪያም ሳይለይ ጌታ ለሕዝቡ ይፈርዳል።


ኢየሱስ ሰው ሆኖ በዚህ ምድር በኖረበት ጊዜ ከሞት ሊያድነው ወደሚችል አምላክ በታላቅ ጩኸትና በብዙ እንባ ጸሎትንና ልመናን አቀረበ፤ በትሕትና ራሱን ታዛዥ በማድረጉ እግዚአብሔር ጸሎቱን ሰማው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች