Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 2:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በሰማይ ዙፋኑ ላይ የሚቀመጠው ይስቅባቸዋል፤ በከንቱ ሐሳባቸውም ጌታ ያፌዝባቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በሰማይ ዙፋን ላይ የተቀመጠው ይሥቃል፤ ጌታም ይሣለቅባቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በሰማያት የሚቀመጠውም እርሱ ይሥቃል፥ ጌታም ይሣለቅባቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በሰ​ማይ የሚ​ኖር እርሱ ይሥ​ቅ​ባ​ቸ​ዋል። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይሣ​ለ​ቅ​ባ​ቸ​ዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 2:4
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለ እርሱ እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ የጽዮን ድንግል ትንቅሃለች፤ ታፌዝብሃለች፤ አንተ እየሸሸህ ሳለህ፥ የኢየሩሳሌም ልጃገረዶች ከኋላህ ሆነው ራሳቸውን ይነቀንቁብሃል።


እግዚአብሔር በተቀደሰ መቅደሱ ነው፤ ዙፋኑም በሰማይ ነው፤ የሰውን ልጆች ይመለከታል። አተኲሮም በማየት ዐይኖቹም ይመረምሩአቸዋል።


አምላካችን በሰማይ ነው፤ እርሱ የፈቀደውን ሁሉ ያደርጋል።


እግዚአብሔር ሆይ! ዙፋንህ በሰማይ ወደ ሆነው ወደ አንተ እመለከታለሁ።


ክፉዎች ሰዎች የሚጠፉበት ቀን እንደ ተቃረበ ስለሚያውቅ እግዚአብሔር በእነርሱ ይስቃል።


እግዚአብሔር የሕዝቡን ጠላቶች ስለ ሰባበራቸው ከምንጊዜውም ይልቅ በፍርሃት ተጨነቁ፤ እግዚአብሔርም ስለ ጠላቸው ፈጽሞ ያፍራሉ።


እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ግን በእነርሱ ላይ ትስቃለህ፤ አሕዛብን ሁሉ ትንቃለህ።


አምላክ ሆይ! መጠጊያዬ ስለ ሆንክ በአንተ እተማመናለሁ።


ከሰማያት በላይ ወዳለው ሰማይ ለሚወጣው ዘምሩ፤ በሚያስገመግም ብርቱ ድምፅ ሲናገርም አድምጡት።


ስለዚህም መከራ በእናንተ ላይ በሚደርስባችሁ ጊዜ እስቅባችኋለሁ፤ ችግር በሚደርስባችሁም ጊዜ አፌዝባችኋለሁ።


እግዚአብሔር ከምድር ክበብ በላይ ዙፋኑን ዘርግቶ መቀመጡን ሰማይን እንደ መጋረጃ መወጠሩንና፥ እንደ መኖሪያ ድንኳን መዘርጋቱን የምድርም ሕዝቦች እንደ ፌንጣ አነስተኞች መሆናቸውን።


ከፍተኛውና ከሁሉ የላቀው፥ ለዘለዓለም የሚኖር ቅዱሱ እንዲህ ይላል፦ “እኔ በተቀደሰና በከፍተኛ ቦታ፥ እንዲሁም ልባቸው ከተሰበረና መንፈሳቸው ትሑት ከሆኑት ጋር እኖራለሁ፤ ይኸውም ትሑት መንፈሳቸውንና የተሰበረ ልባቸውን ለማደስ ነው።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ ማሳረፊያ ናት፤ ታዲያ ለእኔ ምን ዐይነት ቤት ትሠሩልኛላችሁ? የማርፍበትስ ቦታ ምን ዐይነት ነው?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች