Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 118:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ቸር ስለ ሆነና ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ስለ ሆነ እግዚአብሔርን አመስግኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እግዚአብሔር ቸር ነውና አመስግኑ፤ ፍቅሩም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ሃሌ ሉያ! ጌታን አመስግኑ፥ ቸር ነውና፥ ፍቅሩም ለዘለዓለም ነውና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በመ​ን​ገ​ዳ​ቸው ንጹ​ሓን የሆኑ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕግ የሚ​ሄዱ ብፁ​ዓን ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 118:1
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቸር ስለ ሆነ፥ ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ስለ ሆነ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑ!


እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ፤ ያደረገውንም ሁሉ ለሕዝቦች ንገሩ፤


እግዚአብሔር ቸር ነው፤ ፍቅሩና ታማኝነቱ ዘለዓለማዊ ነው።


ነገር ግን እግዚአብሔር ለሚያከብሩት ሁሉ ፍቅሩን ለዘለዓለም ያሳያቸዋል፤ ቸርነቱም ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተላለፋል።


እግዚአብሔርን አመስግኑ! ቸር ስለ ሆነና ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ስለ ሆነ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑ!


ቸር ስለ ሆነና ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ስለ ሆነ እግዚአብሔርን አመስግኑ!


ቸር ስለ ሆነና ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ስለ ሆነ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑት።


ቸር ስለ ሆነ ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርቡ፤ ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።


በዚህ ቦታ የተድላና የደስታ፥ የሠርግ ዘፈን ድምፅ እንደገና ይሰማል፤ ከምርኮ ለተመለሱትም ቀድሞ የነበራቸውን ንብረታቸውን ስለምመልስላቸው የምስጋና መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ ቤተ መቅደሴ በሚመጡበት ጊዜ፥ ‘የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ እርሱ ቸር ነውና፥ ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ነውና’ እያሉ በከፍተኛ ድምፅ ይዘምራሉ። ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች