Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 112:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እምነቱ ጽኑ ስለ ሆነና በእግዚአብሔርም ስለሚተማመን፥ ክፉ ወሬ አያስደነግጠውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ክፉ ወሬ አያሸብረውም፤ ልቡ እግዚአብሔርን በመተማመን የጸና ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ክፉ ዜናን አይፈራም፥ ልቡ የጸና፥ በጌታም የታመነ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ድሃ​ውን ከም​ድር የሚ​ያ​ነሣ፥ ምስ​ኪ​ኑ​ንም ከመ​ሬት ከፍ ከፍ የሚ​ያ​ደ​ርግ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 112:7
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚያን ጊዜ ቀና ብለህ ያለ ኀፍረት ሁሉን ነገር ታያለህ፤ ያለ ፍርሀትም ጸንተህ መቆም ትችላለህ።


እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ሆኖ ስለሚረዳኝ አልፈራም፤ ከቶ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?


የእግዚአብሔርን ርዳታ ፈለግኹ እርሱም ሰማኝ፤ ከምፈራውም ነገር ሁሉ አዳነኝ።


እንዲሁም በሀብታቸው ብዛት የሚተማመኑና በብልጽግናቸው ብዛት የሚመኩ ክፉ ሰዎች ቢከቡኝስ ለምን እፈራለሁ?


ልቤ ጽኑ ነው፤ አምላክ ሆይ! ልቤ ጽኑ ነው፤ በመልካም ቃና እዘምርልሃለሁ!


ሕዝቦች ሆይ! ዘወትር በእግዚአብሔር ታመኑ፤ እርሱ መጠጊያችን ስለ ሆነ የልባችሁን ሐሳብ ሁሉ ለእርሱ አቅርቡ።


ጻድቃን በእግዚአብሔር ደስ ይበላቸው እርሱንም ከለላ ያድርጉ፤ ልባቸውም ቅን የሆነ ሁሉ ያመስግኑት።


እኔን የሚሰማ ግን ለሕይወቱ ዋስትና ይኖረዋል፤ ምንም የሚያስፈራው ነገር ሳይደርስበት በሰላም ይኖራል።”


ሲድራቅ፥ ሚሳቅና አብደናጎም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “ንጉሥ ሆይ! በዚህ ጉዳይ ላይ ራሳችንን የምንከላከልበት መልስ ልንሰጥህ አያስፈልገንም።


በትዕግሥታችሁ ነፍሳችሁን ታድናላችሁ” አለ።


ስለ ጦርነትና ስለ ሁከት በምትሰሙበት ጊዜም አትደንግጡ፤ አስቀድሞ ይህ ይሆን ዘንድ ይገባል፤ ይሁን እንጂ ፍጻሜው ወዲያውኑ አይሆንም።”


ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ልባችሁ አይጨነቅ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፤ በእኔም እመኑ፤


የእግዚአብሔርን የጸጋ ወንጌል ለማስተማር ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልኩትን የማገልገል ግዴታ ከፈጸምኩ ለሕይወቴ ዋጋ አልሰጠውም፤ ለነፍሴም አልሳሳለትም።


ጳውሎስ ግን “እንደዚህ እያለቀሳችሁ ስለምን ልቤን በሐዘን ትሰብሩታላችሁ? እኔ ስለ ጌታ ኢየሱስ ስም በኢየሩሳሌም ለመታሰር ብቻ ሳይሆን ለመሞትም ዝግጁ ነኝ” ሲል መለሰ።


ስለዚህ እናንተ ሰዎች አይዞአችሁ! እግዚአብሔር ይህንን የነገረኝን ሙሉ በሙሉ እንደሚፈጽም አምነዋለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች