Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 9:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ድንኳናቸውን የሚተክሉትም ሆነ ሰፈር ለቀው ወደ ፊት የሚጓዙት እግዚአብሔር ለሙሴ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 በእግዚአብሔር ትእዛዝ ይሰፍራሉ፤ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ይጓዛሉ፤ እነርሱም በሙሴ አማካይነት የተሰጠውን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይጠብቁ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 በጌታ ትእዛዝ ይሰፍሩ ነበር፥ በጌታም ትእዛዝ ይጓዙ ነበር፥ ጌታ በሙሴ አንደበት እንዳዘዘ የጌታን ትእዛዝ ይጠብቁ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ይሰ​ፍሩ ነበር፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ ይጓዙ ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ ቃል እንደ አዘዘ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ይጠ​ብቁ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 በእግዚአብሔር ትእዛዝ ይሰፍሩ ነበር፥ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ይጓዙ ነበር፥ እግዚአብሔር በሙሴ እጅ እንዳዘዘ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይጠብቁ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 9:23
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚህ ጊዜ ሁሉ ወገኖቻችሁን እስራኤላውያንን የከዳችሁበት ጊዜ የለም፤ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በጥንቃቄ ፈጽማችኋል።


ደመናው በድንኳኑ ላይ ለብዙ ቀኖች ቢቈይ እንኳ ለእግዚአብሔር በመታዘዝ እዚያው ይቈያሉ እንጂ አይንቀሳቀሱም።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል አለው፦ “አካሄድህ እንደኔ ፈቃድ ቢሆን፥ ያዘዝኩህንም ሁሉ ብታደርግ፥ በቤተ መቅደሴ የአስተዳዳሪነትን፥ በአደባባዮቼም የበላይነትን ሥልጣን እሰጥሃለሁ፤ እዚህ ከቆሙት መላእክት ጋር በእኔ ፊት መግባትና መውጣት እንድትችል ባለሟልነትን እሰጥሃለሁ።


የተቀደሰ ቊርባኔንም በኀላፊነት አልጠበቃችሁም፤ እንዲያውም በተሰጣችሁ የኀላፊነት ቦታ ላይ ባዕዳንን መደባችሁበት።’ ”


አንተን የምባርክበትም ምክንያት አባትህ አብርሃም ለእኔ ታዛዥ በመሆን የሰጠሁትን ትእዛዞች፥ ድንጋጌዎችንና ሕጎችን ሁሉ ስለ ጠበቀ ነው።”


እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦


በምክርህ ትመራኛለህ፤ በመጨረሻም በክብር ትቀበለኛለህ።


እግዚአብሔርም ሊኖሩ ወደሚችሉበት ከተማ በትክክለኛ መንገድ መራቸው።


እንዲሁም በሸለቆው ውስጥ እንደሚሄድ የከብት መንጋ የእግዚአብሔር መንፈስ ዕረፍትን ሰጣቸው። ስምህ ይከብር ዘንድ ሕዝብህን በዚህ ዐይነት መራሃቸው።


መላው የእስራኤል ሕዝብ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ከቦታ ወደ ቦታ በመዘዋወር “ሲን” ተብሎ የሚጠራውን ምድረ በዳ ትተው በረፊዲም ሰፈሩ፤ ነገር ግን በዚያ የሚጠጣ ውሃ አልነበረም።


እስራኤላውያንም እግዚአብሔር ለሙሴ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ለመጀመሪያ ጊዜ ጒዞ ጀመሩ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች