ዘኍል 32:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 ይህም የእግዚአብሔር ውሳኔ እግዚአብሔርን በሙሉ ልባቸው ከታዘዙት ከቀኒዛዊው ከየፉኔ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር ማንኛውንም ሰው የሚያጠቃልል ነው። ለእግዚአብሔር ታማኞች ሆነው የተገኙት እነርሱ ብቻ ናቸው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 እግዚአብሔርን በፍጹም ልባቸው ተከትለውታልና፣ ከቄኔዛዊው ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር አንዳቸውም አያዩዋትም።’ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 ዳሩ ግን ለዮፎኔ ልጅ ካሌብና ለነዌ ልጅ ለኢያሱ በእውነት ጌታን ፈጽመው ስለ ተከተሉ ይህ እንዲህ አይሆንም።’ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 እግዚአብሔርን ተከትለዋልና ከእነዚህ፥ ልዩ ከሆነ ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር፤ ምዕራፉን ተመልከት |