Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 31:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ሙሴም ከየነገዱ አንዳንድ ሺህ ሰው በካህኑ በአልዓዛር ልጅ በፊንሐስ መሪነት ወደ ጦርነት ላካቸው፤ ፊንሐስም ከመቅደሱ አንዳንድ ንዋየ ቅድሳትንና ለጦርነት መቀስቀሻ (ክተት) የሚሆን መለከት በእጁ ይዞ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ሙሴም የቤተ መቅደሱን ንዋየ ቅድሳትና ምልክት መስጫ የሆኑትን መለከቶች ከያዘው ከካህኑ ከአልዓዛር ልጅ ከፊንሐስ ጋራ ከየነገዱ አንዳንድ ሺሕ ሰው ለጦርነት ላከ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ሙሴም ከየነገዱ አንድ አንድ ሺህ ወደ ጦርነት ላከ፤ እነርሱንና የካህኑን የአልዓዛርን ልጅ ፊንሐስን ወደ ጦርነት ላካቸው፤ የመቅደሱንም ዕቃ የሚነፋውንም የማስጠንቀቂያ መለከት በእጁ ሰጠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ሙሴም ከየ​ነ​ገዱ አንድ ሺህ ከሠ​ራ​ዊ​ታ​ቸ​ውና ከካ​ህኑ ከአ​ሮን ልጅ ከአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ ከፊ​ን​ሐስ ጋር ሰደደ፤ ንዋ​ያተ ቅድ​ሳ​ቱና ምል​ክት መስጫ መለ​ከ​ቶ​ችም በእ​ጆ​ቻ​ቸው ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ሙሴም ከየነገዱ አንድ አንድ ሺህ ወደ ጦርነት ሰደደ፤ እነርሱንና የካህኑን የአልዓዛርን ልጅ ፊንሐስን ወደ ጦርነት ሰደዳቸው፤ የመቅደሱንም ዕቃ የሚነፋውንም መለከት በእጁ ሰጠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 31:6
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኦርዮም እንዲህ ሲል መልስ ሰጠ፤ “የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎች በድንኳን ሰፍረው በጦር ሜዳ ይገኛሉ፤ የቃል ኪዳኑም ታቦት ከእነርሱ ጋር ነው፤ የጦር አለቃዬ ኢዮአብና የእርሱም የጦር መኰንኖች በሜዳ ሰፍረዋል፤ ታዲያ እኔ ወደ ቤቴ ሄጄ መብላት፥ መጠጣት፥ ከሚስቴም ጋር መተኛት እንዴት ይቻለኛል? ይህን የመሰለ ነገር ከቶ እንደማላደርግ በአንተ ሕይወት እምላለሁ!”


ቡቂ የአቢሹዓ ልጅ፥ አቢሹዓ የፊንሐስ ልጅ፥ ፊንሐስ የአልዓዛር ልጅ፥ አልዓዛር የሊቀ ካህናቱ የአሮን ልጅ ነው።


ድንኳኑንና በውስጡ ያሉትን ዕቃዎች ሁሉ እኔ በማሳይህ ዕቅድ መሠረት ሥሩት።


እነርሱ ግን ሌላው ቀርቶ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦትም ሆነ ሙሴ ከሰፈር ሳይነሡ ወደ ተራራማይቱ አገር ለመዝመት ደፍረው ተነሡ።


ስለዚህ ከብዙ ሺህ እስራኤላውያን መካከል ከያንዳንዱ ነገድ አንዳንድ ሺህ ተውጣጥቶ ዐሥራ ሁለት ሺህ የታጠቀ ሠራዊት ለጦርነት ተዘጋጀ።


ጦርነት ከመጀመራችሁ በፊት ካህኑ ወደ ሠራዊቱ ቀርቦ እንዲህ ይበል፦


ይህም ከመሆኑ በፊት የእስራኤል ሕዝብ የካህኑን የአልዓዛርን ልጅ ፊንሐስን በገለዓድ ምድር ወደሚገኙት ወደ ሮቤል፥ ወደ ጋድና በምሥራቅ ወደሚኖሩት የምናሴ ነገዶች ሕዝብ ላኩት፤


ሳኦልም ካህኑን አኪያን “ኤፉዱን ይዘህ ና” አለው። በዚያን ቀን ካህኑ አኪያ ኤፉድ ለብሶ በእስራኤል ሕዝብ ፊት ነበር፤


ዳዊትም ሳኦል አደጋ ሊጥልበት ማቀዱን በሰማ ጊዜ ካህኑን አብያታርን “ኤፉዱን ይዘህ ና!” አለው።


ወሬ ነጋሪውም “እስራኤላውያን ድል ሆነው ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ ይህም ሽንፈት በእኛ ላይ መድረሱ እጅግ አሠቃቂ ነው፤ ከዚህም ሁሉ ጋር ልጆችህ ሖፍኒና ፊንሐስ ተገደሉ፤ የእግዚአብሔርም የቃል ኪዳን ታቦት ተማረከች” ሲል መለሰለት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች