Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 27:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 “የጸሎፍሐድ ሴቶች ልጆች የጠየቁት ትክክል ነገር ነው፤ ስለዚህ በአባታቸው ዘመዶች መካከል ርስት ስጣቸው፤ የአባታቸው ድርሻ ወደ እነርሱ ይተላለፍ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “የሰለጰዓድ ልጆች ጥያቄ ትክክል ነው፤ በርግጥ በአባታቸው ዘመዶች መካከል ድርሻቸውን ርስት አድርገህ ልትሰጣቸው ስለሚገባ የአባታቸውን ድርሻ ለእነርሱ አስተላልፍላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 “የሰለጰዓድ ልጆች ትክክለኛ ነገር ተናግረዋል፤ በአባታቸው ወንድሞች መካከል የርስት ድርሻ ስጣቸው፤ የአባታቸውን ርስት ወደ እነርሱ ይተላለፍ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 “የሰ​ለ​ጰ​ዓድ ልጆች እው​ነት ተና​ግ​ረ​ዋል፤ በአ​ባ​ታ​ቸው ወን​ድ​ሞች መካ​ከል የር​ስት ድርሻ ስጣ​ቸው፤ የአ​ባ​ታ​ቸ​ውን ርስት ለእ​ነ​ርሱ ስጥ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 የሰለጰዓድ ልጆች እውነት ተናግረዋል፤ በአባታቸው ወንድሞች መካከል የርስት ድርሻ ስጣቸው፤ የአባታቸውን ርስት ለእነርሱ አሳልፈህ ስጥ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 27:7
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሁላችሁም በኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ስለ ሆናችሁ በአይሁዳዊና በግሪካዊ፥ በአገልጋይና በጌታ፥ በወንድና በሴት መካከል ምንም ልዩነት የለም።


በመካከላችሁ ያሉትን አባቶቻቸውና እናቶቻቸው የሞቱባቸውን ልጆች ተዉአቸው እኔ በሕይወት አኖራቸዋለሁ። ባሎቻቸው የሞቱባቸውም ሴቶች በእኔ ይተማመኑ።


እነርሱም ወደ ካህኑ አልዓዛር፥ ወደ ነዌ ልጅ ኢያሱና ወደ መሪዎቹ ቀርበው “እንደ ወንዶች ዘመዶቻችን የርስት ድርሻ እንዲሰጠን እግዚአብሔር ሙሴን አዞታል” አሉአቸው። ስለዚህም እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ለእነርሱ ከወንዶች ዘመዶቻቸው ጋር የርስት ድርሻ ተሰጣቸው፤


በተቀደሰ መኖሪያው ያለ አምላክ አባት ለሌላቸው ልጆች አባት ነው፤ ባሎቻቸው ለሞቱባቸውም ሴቶች ጠባቂ ነው።


እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤


ወንድ ልጅ ሳይወልድ የሚሞት ሰው ቢኖር ሴት ልጁ ንብረቱን መውረስ እንደሚገባት ለእስራኤል ሕዝብ አስታውቅ።


ስለዚህ እግዚአብሔር ‘የጸሎፍሐድ ሴቶች ልጆች ከገዛ ነገዳቸው ወገን እስከ ሆነ ድረስ የወደዱትን ማግባት ይችላሉ’ ይላል።


ስለዚህ ሙሴ ለእስራኤል ሕዝብ ከእግዚአብሔር የተቀበለውን ትእዛዝ እንዲህ ሲል አስተላለፈ፤ “የምናሴ ነገድ የተናገሩት ሁሉ ትክክል ነው፤


በዓለም ላይ የኢዮብን ሴቶች ልጆች በቊንጅና የሚወዳደሩአቸው ሴቶች አልነበሩም፤ አባታቸውም ከወንድሞቻቸው ጋር ርስት አካፈላቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች