Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 27:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ሙሴ እጆቹን በኢያሱ ራስ ላይ ጭኖ ከዚያ በኋላ የእርሱ ተተኪ መሆኑን በግልጥ አስታወቀ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ከዚያም እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ባዘዘው መሠረት እጁን በራሱ ላይ ጭኖ ሾመው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ጌታም በሙሴ እንደ ተናገረ፥ እጁን በእርሱ ላይ ጫነበት፥ አዘዘውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እንደ አዘ​ዘው፥ እጁን በላዩ ጫነ​በ​ትና፥ ሾመው፤ አዘ​ዘ​ውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 እግዚአብሔርም በሙሴ እንደ ተናገረ፥ እጁን በላዩ ጫነበት፥ አዘዘውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 27:23
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይልቅስ ለኢያሱ አስፈላጊውን መመሪያ ስጠው፤ በማበረታታትም አጠንክረው፤ ሕዝቡ ተሻግረው ይህችን የምታያትን ምድር ይወርሱ ዘንድ የሚመራቸው እርሱ ነው።’


በካህኑ በአልዓዛርና በመላው ማኅበር ፊት እንዲቆም አድርገው፤ በእነርሱም ሁሉ ፊት የአንተ ተተኪ መሆኑን አስታውቅ።


እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “በመንፈስ ጠንካራ የሆነውን የነዌን ልጅ ኢያሱን ውሰድና እጆችህን በራሱ ላይ ጫን፤


ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ ኢያሱንም ወስዶ በካህኑ በአልዓዛርና በመላው ማኅበር ፊት እንዲቆም አደረገው፤


እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤


ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር የነዌን ልጅ ኢያሱን እንዲህ ሲል አዘዘው፦ “በርታ ደፋርም ሁን፤ እኔ ልሰጣቸው በመሐላ ቃል ወደገባሁላቸው ምድር የእስራኤልን ሕዝብ መርተህ ታገባለህ፤ እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ።”


ሙሴ የእርሱ ተተኪ እንዲሆን እጆቹን በመጫን ሹሞት ስለ ነበር የነዌ ልጅ ኢያሱ በጥበብ የተሞላ ሆነ፤ የእስራኤልም ሕዝብ ለኢያሱ ታዘዘለት፤ እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት የሰጣቸውንም ትእዛዝ ጠበቁ።


“ከዚህም ቀጥሎ ኢያሱን እንዲህ ስል መከርኩት፤ ‘እግዚአብሔር አምላካችሁ ሲሖንና ዖግ ተብለው በሚጠሩት በሁለት ነገሥታት ያደረገውን በዐይናችሁ አይታችኋል፤ ምድሩን በምትወርሱበት በማንኛውም ሕዝብ ላይ ይህንኑ ተመሳሳይ ድርጊት ይደግመዋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች