Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 26:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ሙሴና ካህኑ አልዓዛር በዮርዳኖስ አጠገብ ከኢያሪኮ ትይዩ ባለው የሞአብ ሜዳ ሕዝቡን ሰብስበው እንዲህ አሉአቸው፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ስለዚህ ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ከኢያሪኮ ማዶ በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው በሞዓብ ሜዳ ለሕዝቡ እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ሙሴና ካህኑ አልዓዛር በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በሞዓብ ሜዳ ላይ እንዲህ ብለው ተናገሩአቸው፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ሙሴና ካህኑ አል​ዓ​ዛ​ርም በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ በኢ​ያ​ሪኮ ፊት ለፊት በሞ​ዓብ ሜዳ ላይ እን​ዲህ ብለው ነገ​ሩ​አ​ቸው፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ሙሴና ካህኑ አልዓዛር በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በሞዓብ ሜዳ ላይ፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 26:3
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እስራኤላውያን ጒዞአቸውን በመቀጠል ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምሥራቅና በኢያሪኮ ትይዩ በሚገኘው በሞአብ ሜዳ ላይ ሰፈሩ።


“እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ኻያና ከኻያ ዓመት በላይ ዕድሜ ያላቸውን ሰዎች ሁሉ ቈጠሩ።” ከግብጽ ምድር የወጡትም እስራኤላውያን እነዚህ ነበሩ፦


ሙሴና አልዓዛር በኢያሪኮ ትይዩ ከዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ባለው በሞአብ ሜዳ እስራኤላውያንን በቈጠሩበት ጊዜ የመዘገቡአቸው የጐሣ መሪዎች እነዚህ ነበሩ።


ከዮርዳኖስ ማዶ በኢያሪኮ ትይዩ በሞአብ ሜዳ ላይ ሰፍረው ወደነበሩት ወደ ሙሴና ወደ አልዓዛር እንዲሁም ወደ መላው ማኅበር አመጡአቸው።


ከዓብሪም ተራራዎች ተነሥተው በመጓዝ በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ለፊት ባለው በሞአብ ሜዳ ሰፈሩ።


በኢያሪኮ ትይዩ ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ ባለው በሞአብ ሜዳ ላይ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦


ሙሴም ከሞአብ ሜዳዎች ተነሥቶ ወደ ነቦ ተራራ ወጣ፤ ከኢያሪኮም በስተምሥራቅ ወዳለው ወደ ፒስጋ ተራራ ጫፍ ደረሰ፤ ከዚያም እግዚአብሔር ምድሪቱን በሙሉ አሻግሮ እንዲመለከት አደረገው፤ ይኸውም ከገለዓድ ግዛት አንሥቶ በስተ ሰሜን በኩል እስካለው እስከ ዳን ከተማ፥


እግዚአብሔርም ከቤትፐዖር ከተማ ፊት ለፊት በሞአብ አገር በሚገኘው ሸለቆ ቀበረው፤ ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ እርሱ የተቀበረበትን ትክክለኛ ቦታ ለይቶ የሚያውቅ የለም።


የእስራኤልም ሕዝብ የሐዘኑ ጊዜ እስከሚያበቃ ድረስ ለሙሴ በማዘን ሠላሳ ቀን በሞአብ ሜዳ አለቀሱለት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች