Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 23:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እርሱም ተመልሶ ሲሄድ ባላቅ ከሞአብ መሪዎች ጋር በዚያው በሚቃጠለው መሥዋዕት አጠገብ እንደ ቆመ አገኘው፤ ባላቅም እግዚአብሔር ምን እንደ ነገረው ጠየቀው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እርሱም ተመልሶ ሲሄድ ባላቅን ከመላው የሞዓብ አለቆች ጋራ በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ አገኘው፤ ባላቅም፣ “እግዚአብሔር ምን አለ?” ሲል ጠየቀው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ወደ እርሱም መጣ፥ እነሆም፥ እርሱ ከእርሱም ጋር የሞዓብ ሹማምንቶች በሚቃጠለው መሥዋዕቱ ዘንድ ቆመው ነበር፤ ባላቅም፦ “ጌታ የተናገረው ምንድነው?” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ወደ እር​ሱም መጣ፤ እነሆ፥ እርሱ ከእ​ር​ሱም ጋር የሞ​ዓብ አለ​ቆች በመ​ሥ​ዋ​ዕቱ ዘንድ ቆመው ነበር፤ ባላ​ቅም በለ​ዓ​ምን አለው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምን አለ?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ወደ እርሱም መጣ፥ እነሆም፥ እርሱ ከእርሱም ጋር የሞዓብ አለቆች በመሥዋዕቱ ዘንድ ቆመው ነበር፤ ባላቅም፦ እግዚአብሔር የተናገረው ምንድር ነው? አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 23:17
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዘግየት ብሎም ንጉሥ ሴዴቅያስ መልእክተኛ ልኮ አስወሰደኝና በቤተ መንግሥቱ በግል ሲያነጋግረኝ “ከእግዚአብሔር የተነገረህ የትንቢት ቃል አለን?” ብሎ ጠየቀኝ። “አዎ፥ አለ!” ብዬ ንግግሬን በመቀጠል “አንተ ለባቢሎን ንጉሥ ተላልፈህ ትሰጣለህ” አልኩት።


እግዚአብሔርም በለዓምን በዚያ ተገናኘው፤ የሚናገረውንም መልእክት ሰጥቶ ወደ ባላቅ ተመልሰህ እንዲህ በለው አለው።


በለዓምም እንዲህ ሲል ትንቢት ተናገረ፤ “የጺጶር ልጅ ባላቅ ሆይ፥ ወደዚህ ቀረብ ብለህ የምነግርህን ሁሉ ስማ፤


በለዓምም “እኔ እግዚአብሔር የነገረኝን ብቻ እንደማደርግ ቀደም ብዬ አስታውቄህ አልነበረምን?” አለው።


ዔሊም “እግዚአብሔር የነገረህ ቃል ምንድን ነው? ከእኔ ምንም ነገር አትደብቅ፤ አንዳች ነገር ብትደብቅ እግዚአብሔር በአንተ ላይ ብርቱ ቅጣት ያምጣብህ” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች