Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 17:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እነርሱንም ወደ መገናኛው ድንኳን ወስደህ አንተን በማነጋግርበት ስፍራ በታቦቱ ፊት ለፊት አኑራቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በትሮቹንም እኔ ከአንተ ጋራ በምገናኝበት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ከምስክሩ ፊት ለፊት አስቀምጣቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እኔ ከእናንተ ጋር በምገናኝበት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ፊት ለፊት አኑራቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እኔ ለእ​ና​ንተ በም​ገ​ለ​ጥ​በት በዚያ በመ​ገ​ና​ኛው ድን​ኳን ውስጥ በም​ስ​ክሩ ፊት አኑ​ራ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እኔ ከእናንተ ጋር በምገናኝበት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ፊት አኑራቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 17:4
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከእርሱም ጥቂቱን ወስደህ በመውቀጥ ካላምከው በኋላ ወደ ድንኳኑ ወስደህ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት እርጨው፤ ይህንንም ዕጣን ፍጹም የተቀደሰ እንዲሆን አድርግ።


ይህንንም መሠዊያ ከቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ለፊት ከተሰቀለው መጋረጃ ውጪ አኑረው፤ እኔም በዚያ ለአንተ እገለጥልሃለሁ፤


እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የአሮንን በትር በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት መልሰህ አኑረው፤ ዐመፀኞች የሆኑ እስራኤላውያን በእኔ ላይ ማጒረምረማቸውን ካልተዉ እንደሚሞቱ ማስጠንቀቂያ ሆኖ ይቀመጥ።”


በሌዊ ነገድ ስም በቀረበውም በትር ላይ የአሮንን ስም ጻፍበት፤ ስለያንዳንዱ ነገድ መሪ አንድ በትር ይቅረብ።


ሙሴ በትሮቹን ሁሉ ወስዶ በድንኳኑ ውስጥ በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ለፊት አኖራቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች