Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 15:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ስለ ስእለት ወይም ስለ አንድነት አንድ ወይፈን ለሚቃጠል ቊርባን ወይም መሥዋዕት በምታቀርብበት ጊዜ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “ ‘አንዱን ወይፈን ለተለየ ስእለት ወይም ለኅብረት የሚቀርብ የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም የዕርድ መሥዋዕት አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር በምታዘጋጁበት ጊዜ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ለሚቃጠልም መሥዋዕት ወይም ለሌላ መሥዋዕት ወይም ስእለትን ለመፈጸም ወይም ለአንድነት መሥዋዕት ወይፈንን ለጌታ ብታዘጋጅ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት፥ ወይም ለሌላ መሥ​ዋ​ዕት፥ ወይም ስእ​ለ​ትን ለመ​ፈ​ጸም፥ ወይም ለደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ከላም ወገን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብታ​ዘ​ጋጅ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ለሚቃጠልም መሥዋዕት ወይም ለሌላ መሥዋዕት ወይም ስእለትን ለመፈጸም ወይም ለደኅንነት መሥዋዕት ወይፈንን ለእግዚአብሔር ብታዘጋጅ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 15:8
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ማንኛውም ሰው ከቀንድ ከብቱ ለእግዚአብሔር የአንድነት መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ ነውር የሌለበትን አንድ ኰርማ ወይም ላም መርጦ ያምጣ።


ይኸውም ከቀንድ ከብቱ መካከል አንዱን ለሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረብ ቢፈልግ ምንም ነውር የሌለበትን ኰርማ መርጦ ያምጣ፤ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት የሰመረ መሥዋዕት ይሆንለት ዘንድ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ በር በኩል ያቅርበው።


ያም ሰው የእንስሳውን ሆድ ዕቃና የኋላ እግሮቹን በውሃ ይጠብ፤ ካህኑም መሥዋዕቱን በሙሉ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው፤ ይህም የሚቃጠል መሥዋዕት ነው። የዚህ ዐይነቱ መሥዋዕት መዓዛ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል።


ይህ የሚቃጠል መሥዋዕት በመሆኑ የአሮን ልጆች በሚቃጠለው መሥዋዕት መሠዊያ ላይ ያቃጥሉት፤ ይህ ዐይነቱ መሥዋዕት መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነው።


ማንም ሰው ስእለት ተፈጽሞለት ወይም የበጎ ፈቃድ ስጦታ አድርጎ የአንድነት መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ቢያቀርብ፥ ተቀባይነት ማግኘት እንዲችል፥ እንስሳው ምንም ነውር የሌለበት ይሁን።


ቀጥሎም አንድ ወይፈንና ለእህል ቊርባን የተመደበውን በዘይት የተለወሰ ዱቄት ይውሰዱ፤ አንተም ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚቀርብ አንድ ወይፈን ውሰድ፤


ለመጠጥ ቊርባን የሊትር አንድ ሦስተኛ የወይን ጠጅ ታቀርባለህ፤ ይህም ሁሉ መሥዋዕት መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል፤


ከወይፈኑ ጋር ሦስት ኪሎ በግማሽ ሊትር ዘይት የተለወሰ ምርጥ ዱቄት የእህል ቊርባን አቅርብ።


እንዲህ ዐይነቱ ስሕተት የተፈጸመው በማኅበሩ አለማወቅ ከሆነ አንድ ወይፈን አምጥተው መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው ያቅርቡት፤ ከእርሱም ጋር ተገቢውን የእህልና የወይን ጠጅ ቊርባን ያቅርቡ፤ በተጨማሪም አንድ ተባዕት ፍየል ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት አድርገው ያቅርቡ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች