Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 15:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 አውራ በግ መሥዋዕት ሆኖ በሚቀርብበት ጊዜ ደግሞ በአንድ ሊትር ተኩል የወይራ ዘይት የተለወሰ ሁለት ኪሎ ዱቄት አቅርቡ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 “ ‘ከአውራ በግ ጋራ በሂን ሢሶ ዘይት የተለወሰ የኢፍ ሁለት ዐሥረኛ ልም ዱቄት የእህል ቍርባን አዘጋጁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ለአንዱም አውራ በግ የኢን መስፈሪያ ሢሶ በሆነ ዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ የሆነ መልካም ዱቄት ለእህል ቁርባን እንዲሆን ታዘጋጃለህ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ለአ​ን​ዱም አውራ በግ የሚ​ቃ​ጠል ቍር​ባን ወይም መሥ​ዋ​ዕት ባደ​ረ​ጋ​ችሁ ጊዜ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ሢሶ በሆነ ዘይት የተ​ለ​ወሰ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ መል​ካም ዱቄት ለእ​ህል ቍር​ባን ታዘ​ጋ​ጃ​ላ​ችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6-7 ለአንዱም አውራ በግ ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን የኢን መስፈሪያ ሢሶ በሆነ ዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ ሁለት እጅ መልካም ዱቄት ለእህል ቍርባን ታዘጋጃለህ፤ የኢን መስፈሪያ ሢሶም የወይን ጠጅ ለመጠጥ ቍርባን ታቀርባለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 15:6
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንግዲህ እንደዚህ ያለውን መሥዋዕት የሚያቀርብ ሰው ሁሉ በሩብ ሊትር ዘይት የተለወሰ አንድ ኪሎ ምርጥ ዱቄት የእህል ቊርባንም ማቅረብ አለበት፤


አንድ ሰው ለእግዚአብሔር የሚያቀርበው መባ ፍየል ከሆነ፥ በእግዚአብሔር ድንኳን ፊት ያቅርበው፤


እንዲሁም ለያንዳንዱ ጠቦት ለመጠጥ ቊርባን የሚሆን ሩብ ሊትር የወይን ጠጅ ከሚቃጠል ቊርባን ወይም መሥዋዕት ጋር ታቀርባላችሁ።


ለመጠጥ ቊርባን የሊትር አንድ ሦስተኛ የወይን ጠጅ ታቀርባለህ፤ ይህም ሁሉ መሥዋዕት መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች