Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 15:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 ስለዚህ መላው ማኅበር ከሰፈር አውጥተው እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት በድንጋይ ወግረው ገደሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 ስለዚህ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ማኅበሩ ሰውየውን ከሰፈር አውጥቶ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ወገረው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 ማኅበሩም ሁሉ ከሰፈሩ ወደ ውጭ አውጡት፥ ጌታም ሙሴን እንዳዘዘው በድንጋይ ወግረው ገደሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 ማኅ​በ​ሩም ሁሉ ከሰ​ፈሩ ወደ ውጭ አወ​ጡት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው በድ​ን​ጋይ ወገ​ሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 ማኅበሩም ሁሉ ከሰፈሩ ወደ ውጭ አውጡት፥ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ወገሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 15:36
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሁለቱም የሐሰት ምስክሮች ተነሥተው “ናቡቴ እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድቦአል” ብለው በሕዝቡ ፊት በሐሰት መሰከሩበት፤ ስለዚህም ከከተማይቱ ውጪ በመውሰድ በድንጋይ ወግረው ገደሉት።


“ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ ብለህ ንገር፦ ከእናንተም ሆነ ወይም በመካከላችሁ ከሚኖሩት የውጪ አገር ተወላጆች ውስጥ፥ ማንም ሰው ሞሌክ ተብሎ ለሚጠራው ባዕድ አምላክ ከልጆቹ አንዱን አሳልፎ ሰጥቶ ቢገኝ መላው የእስራኤል ሕዝብ በድንጋይ ወግሮ ይግደለው።


ከዚያን በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን “ሰውየው መገደል አለበት፤ መላው ማኅበር ከሰፈር አውጥተው በድንጋይ ወግረው ይግደሉት” አለው።


እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤


የከተማይቱም ሰዎች ሁሉ በድንጋይ ወግረው ይግደሉት፤ በዚህም ዐይነት ይህን ክፉ ነገር ታስወግዳላችሁ፤ በእስራኤልም የሚኖር ሁሉ ይህን ሁኔታ ሰምቶ ይፈራል።


ኢያሱም “ይህን ሁሉ መከራ በእኛ ላይ ያመጣህብን ስለምንድን ነው? እነሆ! በአንተም ላይ ዛሬ እግዚአብሔር መከራን ያመጣብሃል!” አለው። ከዚህ በኋላ ሕዝቡ ሁሉ ዓካንን በድንጋይ ወግረው ገደሉት፤ ቤተሰቡንም በድንጋይ ወግረው ንብረቱን ሁሉ አቃጠሉ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች