Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 15:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እንዲሁም ግማሽ ሊትር የወይን ጠጅ የመጠጥ ቊርባን አድርገህ ታቀርባለህ፤ ይህም ለእግዚአብሔር መልካም መዓዛ የሚሆን የሚቃጠል መሥዋዕት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እንዲሁም ለመጠጥ ቍርባን የሚሆን ግማሽ ሂን የወይን ጠጅ አቅርቡ፤ ይህም በእሳት የሚቀርብና ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ለጌታም መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርገህ፥ የኢን መስፈሪያ ግማሽ የወይን ጠጅ ለመጠጥ ቁርባን ታቀርባለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በእ​ሳት ለተ​ደ​ረገ ቍር​ባን፥ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ግማሽ ወይን ለመ​ጠጥ ቍር​ባን ታቀ​ር​ባ​ለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን በእሳት ለተደረገ ቍርባን፥ የኢን መስፈሪያ ግማሽ የወይን ጠጅ ለመጠጥ ቍርባን ታቀርባለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 15:10
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንዲሁም ለያንዳንዱ ጠቦት ለመጠጥ ቊርባን የሚሆን ሩብ ሊትር የወይን ጠጅ ከሚቃጠል ቊርባን ወይም መሥዋዕት ጋር ታቀርባላችሁ።


ደግሞም እርሾ ሳይነካው የተጋገረ አንድ መሶብ እንጀራ፥ በወይራ ዘይት ከተለወሰ ዱቄት የተጋገረ ውፍረት ያለው ኅብስት፥ በወይራ ዘይት የተቀቡ ስስ ቂጣዎች ጭምር ከሚቀርበው ከእህል ቊርባንና ከመጠጥ መባ ጋር አብሮ ይቅረብ።


ከወይፈኑ ጋር ሦስት ኪሎ በግማሽ ሊትር ዘይት የተለወሰ ምርጥ ዱቄት የእህል ቊርባን አቅርብ።


“ ‘እንግዲህ ከእያንዳንዱ ወይፈን፥ አውራ በግ፥ የበግ ወይም የፍየል ጠቦት ጋር የሚቀርበው የእህል ቊርባን ይህ ነው፥


ጡት ካስጣለችውም በኋላ ወደ ሴሎ ይዛው ወጣች፤ ከእርሱም ጋር የሦስት ዓመት ኰርማ ዐሥር ኪሎ ዱቄትና አንድ አቁማዳ ሙሉ የወይን ጠጅ ይዛ ሄደች፤ ሳሙኤልንም ገና በልጅነቱ በሴሎ ወደሚገኘው ወደ እግዚአብሔር ቤት ወሰደችው፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች